2011-01-14 14:39:43

ብራዚል፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ


በብራዚል ደቡባዊ ምሥራቅ ክልል በምተገኘው ሪዮ ደ ጃነሮ ግዛት የጣለው ኃይለኛ ዝናብ ያስከተለው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ፣ በሰው እና በንብረት ላይ አቢይ ጉዳት እንዳስከተለ ሲገለጥ፣ በተከሰተው የጎፍር መጥለቅለቅ አደጋ ሳቢያ RealAudioMP3 ከ 350 በላይ የሚገመት ሕዝብ ለሞት አደጋ መጋለጡ ለማወቅ ሲቻል፣ በኖቫ ፍሪቡርጎ ክልል ደግሞ 150 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

የሪዮ ደ ጃኔሮ ክልል አስተዳዳሪ ሰርጆ ካብራል ከብራዚል ማእከላዊ መንግሥት አስቸኳይ መሠረታዊ እርዳታ ይቀርብ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ለማወቅ ሲቻል፣ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ዲልማ ሩሰፍ በመከላከያ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ተሸኝተው ዛሬ በጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ እጅግ የተጠቃውን ክልል እና ሕዝብ እንደጎበኙ ከብራዚል የሚሰራጩ ዜናዎች ያመለክታሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በብራዚል የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በተለያዩ የተራድኦ ድርጅቶቸዋ አማካኝነት ያስቸኳይ እርዳታ አቅርቦት መርሃ ግብር እያከናወነች መሆንዋ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የሪዮ ደ ጃኔየሮ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ኣቡነ ኦራኒ ዥዋው ተምፐስታ በማረጋገጥ፣ የጣለው ኃይለኛው ዝናብ ኮረብታማው ክልል በእጅጉ እንዳጠቃ እና ተረሶፖሊስ፣ ፐትሮፖሊስ እና ኖቫ ፍሪቡርጎ ከተሞችን ለከፋ አደጋ ማጋለጡ ጠቅሰው፣ የክልሉ ብፁዓን ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፊሊፖ ሳንቶሮ፣ ብፁዕ አቡነ ኤድነይ ጉቨአ ማቶሶ የተጎዳውን ህዝብ በመጎብኘት በካሪታስ የሚጠራው እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስያን የተራድኦ ማህበር በብራዚል በሚገኘው ቅርንጫፉ አማካኝነት የሚቀርበ እርዳታ በማቀነባበር ላይ እንደሚገኙ ገልጠዋል።

የክልሉ ኃይለኛው ዝናብ አዘል የአየሩ ጸባይ ሻል እያለ መሆኑ ጠቅሰው፣ ለሞቱት እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበላቸው ቤተሰቦቻቸውን እንዲያጽናና ተማጥነው፣ ለተጎዳው ሕዝብ እንዲጸለይ አደራ በማለት ሁሉም ለድጋፍ እና ለትብብር እንዲነቃ አደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.