2011-01-14 14:40:54

ስፐይን፣ ለዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ቅድመ ዝግጅት


ሁሌ በየዓመት ከሁሉም አገሮች የተወጣጡ ወጣቶችን በማሰባሰብ ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አስተምህሮ ምክር፣ የሚለገስበት የተለያዩ መንፈሳዊ እና ባህላዊ መርሃ ግብር የሚረጋገጥበት በጠቅላላ እምነት የሚመሰከርበት ኵላዊነት ቤተ ክርስትያን RealAudioMP3 የምታዘጋጀው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እቅድ መሠረት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የዘንድሮው 26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በስፐይን ርእሰ ከተማ ማድሪድ እ.ኤ.አ. ከነሓሴ 16 ቀን እስከ ነሓሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲካሄድ መወሰናቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ለዚህ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ቅድመ ዝግጅት ለማጠናቀቅ የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፅዕ ካርዲናል ስታኒስላው ርይልኮ የማድሪድ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ሩዎኮ ቫረላ የሚመሩት ስብሰባ ከትላንትና በስትያ በማድሪድ ክፍለ ከተማ ኤስኮሪያል መጀመሩ የሚዘከር ሲሆን፣ በዚህ እ.ኤ.አ. ጥር 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በሚጠናቀቀው ስብሰባ የሁሉም አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የምእመናን ጉዳይ እንዲሁም የወጣቶች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ድርገቶች ተጠሪዎቻቸው አማካኝነት እየተሳተፉ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

እ.ኤ.አ. በ1989 ዓ.ም. የሳንቲያጎ ዲ ኮምፖስተላ ሊቀ ጳጳስ እያሉ በስፐይን ካሚኖ ከተማ የዮሓንስ ወንጌል ምዕራፍ 14 ቁጥር 6 “እኔ መንገድ እውነት እና ሕይወት ነኝ” በሚለው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ተመርቶ የተካሄደውን በመዘከር፣ ይኽ በማድሪድ የቅዱስ ሐዋርያት ጳውሎስ ወደ ቆላስያስ በጻፈው መልዕክት ምዕራፍ 2 ቁጥር 7 “በክርስቶስ ጸንታችሁ እና ተመሥርታችሁ በእምነት ጽኑዎች ሁኑ” በሚለው ቃል ተመርቶ የሚካሄደው የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የቀጣቶች ቀን ያለፉት ዓመታ የወጣቶች ቀን ገጠመኝ ኃብት የሚያንጸባርቅ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ሩዎኮ ቫረላ መግለጣቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.