2011-01-12 13:56:34

ዕለታዊ የቤተ ክርስትያን የሊጡርጊያ ባሕረ ሐሳብ


ዕለታዊ ኑሮ የተለያዩ ዓበይት የእምነት አብነት የሆኑት የቤተ ክርስትያን ልጆች የኅልውና ታሪክ እንደሚያረጋግጠው በእግዚአብሔር ጸጋ ድጋፍ እና በጸና እምነት አማካኝነት ሊደረስ ወደ ሚቻለው የቅድስና ሕይወት የሚሸኝ ጉዞ መሆኑ እንደሚረጋገጥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተለያየ ወቅት የቤተክርስትያን ሊጡርጊያ ባሕረ ሐሳብ ከዓበይት በዓለት ባሻገር የሚኖረው ዕለታዊ ኑሮ RealAudioMP3 በማስደገፍ በሰጡት አስተምህሮ በማሳሰብ፣ በተለይ ደግሞ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት እና ጥምቀት ዓበይት በዓላት ከማክበር በኋላ በቤተ ክርስትያን ባሕረ ሐሳብ መሠረት የሚኖረው ዕለታዊ ኑሮ የተቀደሰ ወደ ቅድስና የሚሸኝ የሕይወት ጉዞ ከመሆኑም ባሻገር፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት በማየ ዮርዳኖስ በዮሓንስ መጥምቅ እጅ ሲጠመቅ ከላየ ሰማያት የወረደው ድምጽ ያበሰረውን በመቀበል ዕለታዊ ኑሮአችን በዚህ ጥልቅ መንፈሳዊነት በመኖር እያንዳንድዋን ዕለት በመቀደስ ወደ ቅድስና የምንመራበት ነው። በቤተ ክርስትያን ሊጡርጊያ ባሕረ ሐሳብ አነጋገር፣ ተራ ወቅት ተብሎ የሚጠራ መሆኑም በመጥቀስ፣ ተራ ጊዜ ሲባል ግን ትርጉም የሌለው ልሙድ ማለት እንዳልሆነ እ.ኤ.አ. ጥር 15 ቀን 2006 ዓ.ም. ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ባሳረጉበት ወቅት በሰጡት አስተምህሮ ሲያብራሩ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት ካከበርንበት ሳምንት ወዲህ በቤተ ክርስትያን የሊጡርጊያ ባሕረ ሐሳብ የተገባው ተራ ወቅት፣ ወደ ቅድስና በማቅናት ክርስትያናዊ ሕይወታችንን የምንኖርበት ጊዜ ነው፣ እርሱም የእምነት ሕይወት እና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለን ወዳጅነት፣ ጌታችን መንገድ እውነት እና የሰው ልጅ ሕይወት መሆኑ በቀጣይነት በመኖር በማጣጣም ዳግም በማረጋገጥ የምኖርበት የተባረከ ጊዜ ነው ካሉ በኋል፣ የእግዚአብሔር ቃል ገና ፍጻሜ ላይ ያልደረሰውን ነገር ግን በሙላት የተገለጠውን የእምነት ፍጻሜ መሠረት የእምነት ጉዞአችንን የምናከናውንበት የአዲስ ዓመት ጅማሬ ነው። በዮሓንስ ወንጌል ምዕራፍ 1 ቁጥር 38 የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት መምህር ሆይ የምትኖረው የት ነው? በማለት ላቀረቡት ጥያቄ ጌታችን ሲመልስ አድራሻውን ኑና ኢዩ በማለት ነው የገለጠው። ለአማኞች ክርስቶስ ዘወትር የማይለወጥ የነበረ ያለ የሚኖር መሆኑ በማመን ካለ ማቋረጥ በእምነት በመጓዝ ዕለት በዕለት ኅዳሴ የሚያረጋግጥበት ወደ ክርስቶስ እየቀረበ ከርእርሱ ጋር ያለው ግኑኝነት እየለየ ጥልቅ እያደረገ ያድጋል። ክርስቶስ የማይለወጥ ነው ሲባል ዓለም እና ታሪክ ባለበት ይጸናል ማለት ሳይሆን የሚለወጥ የሚታደስ ነው። ምክንያቱም እርሱ ውኅደት እና የሕይወት ሙላት ሊሰጠን ከእኛ ጋር ለመገናኘት ወደ እኛ የሚመጣ በመሆኑ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ገልጦታል።

እ.ኤ.አ. ጥር 3 ቀን 2010 ዓ.ም. ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ በሰጡት አስተምህሮ፣ ተስፋችን በእግዚአብሔር ነው፣ እንዲህ ሲባል ግን ልሙድ እና ጠቅላይ የሃይምኖት ትርጉም ያለው የዕድል ጽሑፍ ማለት እንዳለሆነ ገልጠው። እኛ በማያዳግም እና በሙላት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ከሰው ልጅ ጋር ለመሆን የገለጠውን ፈቃዱን የታሪኩን ተካፋዮች እንድንሆን ሁላችንን የፍቅር እና የሕይወት መንግሥት ወደ ሆነው መንግሥቱ ሊመራን በፈቀደው እግዚአብሔር እንታመናለን። ይህ አቢይ ተስፋ ሰብአዊ ተስፋችንን ያነቃቃል ያርማልም እንዳሉ ይዘከራል።

እ.ኤ.አ. ጥር 15 ቀን 2006 ዓ.ም. መፈለግ እና ማግኘት በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 1 ከቁጥር 35 እስከ ቁጥር 42 ባለው ንባብ ዘነድ የምናገኛቸው ግሶች ናቸው። እነዚህ ግሶች በትክክል በተረጋገጠ መንገድም ለአዲስ ዓመት መሠረታዊ ትርጉም ናቸው። ለክርስትያን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት መሆን ብቻ በቂ ነው። ከእርሱ ጋር የሚመሠረት ጓደኝነት ሰላምን ያነቃቃል፣ በዕለታዊ ኑሮ ችግር ስቃይ እና ጨለማም ቢፈራረቅብን ውስጣዊ እርጋታ እና እርካታ ይሰጣል። እምነታችን ምንም ነገር ልናይበት በማይቻለው የእግዚአብሔር ኅላዌ የሌላ በሚያስመስለው ድቅድቅ ባለ ጨለማ ሲገኝ፣ ከክርስቶስ ጋር ያለን ወዳጅነት ጓደኝነት ከእግዚአብሔር ፍቅር የሚለየን ምንም ነገር እንደሌለ ያረጋግጥልናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ጠቅሶታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.