2011-01-12 13:57:40

ለመካከለኛው ምሥራቅ ማኅበረ ክርስትያን ድጋፍ


የኤውሮጳ እና የሰሜን አሜሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በቅድስት መሬት ለሚገኙት ውሁዳን ማኅበረ ክርስትያንብ ትብብራቸውን ቅርበታቸው እና ድጋፋቸው ለማረጋገጥ እ.ኤ.አ. ጥር 13 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚያጠቃልሉት ባለፈው ዓመት RealAudioMP3 ጥቅምት ወር እዚህ በቫቲካን የተካሄደው የክርስትና ሃይማኖት ውህደት እና የጋራው ክርስትያናዊ ምስክረነት እና የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት አድማስ ያደረገው አንደኛው የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ መሠረት ያደረገ እ.ኤ.አ. ጥር 9 ቀን 2011 ዓ.ም. የጀመሩት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው እየቀጠሉበት ሲሆን፣ ይኽ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከት በቅድስት መሬት የቅድስት መንበር ንብረት እና ቅዱሳት ሥፍራ አስተዳዳሪ አባ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይህ ዓይነቱ ሐዋርያዊ ጉብኝት በመካከለኛው ምሥራቅ ለሚኖረው ውሁዳን ማኅበረ ክርስትያን እጅግ አስፈላጊ ነው። ሆኖም ግን ይህ ዓይነት ጉብኝት የመካከለኛው ምሥራቅ ፖለቲካዊ ጉዳይ ይለውጣል ማለት ሳይሆን በዚያ ክልል ለሚኖረው ሁሉ በተለይ ደግሞ ማኅበረ ክርስትያንን የሚደገፍ ተግባር ነው ብለዋል።

በመካከለኛው ምሥራቅ ተገኝቶ በዚያ ክልል የሚኖረው የማኅበረ ክርስትያን ገጠመኝ ቀርቦ በመረዳት ክርስትያኖችን የሚያበረታታ የቤተ ክርስትያን ኵላዊነት ባህርይ የሚያረጋግጥ ነው። በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ማኅበረ ክርስትያን ዕለታዊ ኑሮ የተለያየ ችግር የሚፈራረቅበት ከዕለት ወደ ዕለት በብዛት አንጻር ሲታይ እየጎደለ በማኅበራዊ በብሔረ መድረክ በፖሊቲካው እና በኤኮኖሚው ሕይወት ተጨባጭ ምልክት ለማቅረብ እያስቸገረው ነው። ለእነዚህ ጉዳዮች ተጨባጭ መፍትሔ የሚጠይቅ ነው፣ ስለዚህ የኤውሮጳ እና የሰሜን አሜሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሐዋርያዊ ጉብኝት ይኸንን የሚያነቃቃ ነው ብለዋል።

በእስራኤልም ሆነ በፍልስጥኤም ራዝ ገዝ ክልል የተለያዩ ሃይማኖት የጋራ ውይይት መርሃ ግብር ለማረጋገጥ እጅግ አስቸጋሪ ነው፣ ችግሩም ቲዮሎጊያዊ ብቻ ሳይሆን ሥነ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ገጽታ ያለው ነው። የሃይማኖት ነጻነት ጉዳይ የተመለከትንም እንደሆነ ይላሉ አባ ፒዛባላ፣ በእውነቱ በሌሎች የመካከልኛው ምሥራቅ ክልል አገሮች ማለትም በኢራቅ ወይንም በግብጽ የሚታየው ዓይነት ችግር የለብንም ሆኖም ግን ወደ ቅዱሳት ሥፍራ አለ ምንም ችግር መንፈሳዊ ንግደት መፈጸም እና የአምልኮ ነጻነት ከሕሊና እና ሀሳብ ከመግለጥ ነጻነት ጋር ተያይዞ ሲሄድ አይታይም። የመካከለኛው ምሥራቅ ክርስትያን እምነት የተወረሰ ባህል ብቻ ሳይሆን ምንም’ኳ ውሁድ የክልሉ ክፍለ ኅብረተሰብ የሚወክል ቢሆንም ቅሉ፣ የግል ሕይወት ምርጫ እና የግል እና የማኅበራዊነት መለያ ጭምር መሆኑ ለይቶ በመገንዘብ እምነቱን ይኖራል ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.