2011-01-10 15:23:23

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ


ሁለ በሳምንት መገባደጃ የቅድስት መንበር የዜና እና የኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ በመቀጠል ትላትና ቅዱስ አባታችን ድኾች እና ሕፃናት በሚል ርእስ ሥር ባቀረቡት ርእሰ አንቀጽ በዚህ በበዓለ ልደት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እጅግ በድኽነት ከተጠቁት RealAudioMP3 እና በአደገኛ በሽታዎች ተለክፈው በሕክምና የሚገኙትን ሕጻናት ቅርብ በመሆን እ.ኤ.አ. ታህሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ለድኾች የምሳ ግብዣ በማቅረብ እና አብረው በማእድ በመቀመጥ ጥር 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ሮማ ወደ ሚገኘው ጀመሊ ሆስፒታል በመሄድ እዛው በሆስፒታሉ የሕጻናት ሕክምና ክፍል በመጎብኘት በአደገኛ በሽታዎች ከተጠቁት ሕፃናት ጋር በመገናኘት አባታዊ ፍቅር በመግለጥ ያሳዩት ጥልቅ መንፈሳዊነት በዓይነ ሥጋ ትንሽ ተግባር ቢመስልም በመንፈሳዊ ዓይነት ዓቢይ ትርጉም ያለው የእግዚአብሔር ፍቅር እና ጥበቃ የመሰከረ ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ጉብኝት መሆኑ አስረድተዋል።

እግዚአብሔር ፍቅር የሚሰዋ ፍቅር ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እግዚአብሔር ፍቅር ነው በሚል ርእስ ነው የደረስዋት ቀዳሚ አዋዲት መልእክታቸውን አባ ሎምባርዲ በርእሰ አንቀጹ በማስታወስ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናቁትን ድኾችን በማፍቀር እነርሱን መስሎ ለታመሙት በስቃይ ላይ የሚገኙትን ቅርብ በመሆን እና በማቀፍ የገለጠው ፍቅር የሚመሰክር ቃላት ያሰፈሩባት የእወንተኛው ፍቅር ማንነት መግለጫ ዓዋዲት መልእክታቸውን የሚመሰክር ሓዋርያዊ ጉብኘት ነበር ብለዋል።

በዓለ ልደት ብዙውን ጊዜ ትብብር ድጋፍ የሚቀርብበት የሚገለጥበት ቅዱስ ወቅት ነው። ሕፃን ሆኖ ሥጋችን ለብሶ የሚወለደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሕፃናት ታሪክ እና ዕለታዊ ሕይወት ለመገናኘት የሚያስችል፣ በእነርሱ ዘንድ ያለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምስል የምንለይበት ይኸንን የምንጸልይበት የምናከበርበት የምቀድስበትት መሆኑ ገልጠው፣ ቤተ ክርስትያን ይኸንን በመቀደስ እና ፍቅሩንም ተግባራዊ በማድረግ በተለይ ደግሞ የዚህ ፍቅር ተቀዳሚ የሆኑት ሕፃናት የተናቁትን ድኾችን በማገልገል እንደምትኖረው ገልጠው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ይኸንን መስክረዋል እየመሰከሩም ናቸው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.