2011-01-10 15:26:01

ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ፣ ኤውሮጳ ለሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ ተሟጋች እና ተከላካይ


የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ለበዓለ ግልጸት ለእግዚእነ ጀኖቫ በሚገኘው በርእሰ አድባራት ቅዱስ ሎረንዞ ካቴድራል መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት፣ ኤውሮጳ ለሃይማኖት ነጻነት ተሟጓች እና ተከላካይ መሆን ይጠበቅባታል ብለዋል።

ኤውሮጳ የሃይማኖት ነጻነት በመላ ዓለም በእያንዳንዱ አገር ይከበር ዘንድ በተለያዩ መንፍሳዊ ባህላዊ እና ፖለቲካዊ መድረኮች ይኸንን የላቀው ሰብአዊ ክብር ታነቃቃ ዘንድ ጥሪ ሲያቀርቡ፣ በተደጋጋሚ በተለያየ ወቅት እንደቀረበው የልማድ ጥሪ ሳይሆን፣ እሳቸው ያቀረቡት ጥሪ በመላ ዓለም በሚገኙት ማኅበረ ክርስትያን የሚብሰለሰል፣ በክርስትናው እምነታቸው ሳቢያ ለተለያዩ አደጋዎች ተጋልጠው የሚገኙት ማኅበረ ክርስትያን የሚያሰሙት ጥሪ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ በመግለጥ፣ ከሩቅ የመጡት የከዋክብት ተማራማሪዎች እውነተኛው ብቸኛ የሆነውን ንጉሥ የት እንደሚገኝ የሰው ልጅ የእግዚአብሔር መሻት የት እና በማን ላይ ማረፍ እንዳለበት ለመመሥከር የተጓዙት፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት በረት እንደደረሱ በመስገድ የሰጡት ምስክርነት፣ እግዚአብሔርን ለምንሻ የላቀ አብነት መሆኑ አብራርተው፣ የእግዚአብሔር የተሟላ መግለጫ የሰው ልጅ እውነተኛ ደስታ እና ብርሃን የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክርስትናው እምነታቸው ምክንያት ለዘርፈ ብዙ ችግር ተጋልጠው የሚግኙት ማኅበረ ክርስትያን መጽናናት ድጋፍ እና ብርታት ነው ብለዋል።

ክርስትና ማለት ምዕራብ ዓለም ማለት አይደለም፣ ሆኖም ግን የምዕራቡ ዓለም ባህል መለያ መሠረት ነው። ወንጌል የማንም ባህል ተከታይ ሳይሆን በማንም ባህል ሳይታጠር እያንዳንዱን ባህል የሚለውጥ የሚሰብክ የሚያድስ ነው ካሉ በኋላ፣ በስቃይ ላይ የሚገኙት ክርስያኖችን አንርሳ የሃይማኖት ነጻነት ተሟጋቾች እንሁን፣ ኤውሮጳ በዚሁ ጉዳይ ላይ ተቀዳሚ ሚና ትጫወት ዘንድ አደራ እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኤውሮጳ እና የሰሜን አሜሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በቅድስት መሬት ለሚገኙት ክርስትያኖች ትብብራቸውን ቅርበታቸው እና ድጋፋቸው ለማረጋገጥ እ.ኤ.አ. ጥር 13 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚያጠቃልሉት ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር እዚህ በቫቲካን የተካሄደው የክርስትና ሃይማኖት ውህደት እና የጋራው ክርስትያናዊ ምስክረነት እና የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋው ውይይት አድማስ ያደረገው አንደኛው የመካከለኛው ምሥራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ መሠረት ያደረገ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ትላትና መጀመራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.