2011-01-07 12:53:57

ኢራቅ፣ አዲሱ የስደተኞች መተዳደሪያ ደንብ


በኢራቅ የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ ሚኒ. ደንዳር ጃጅማን አል ዶስኪ ባለፈው ሳምነት በኢራቅ የአገር ውስጥ የስደተኞች እና የተፈናቃዮች እርሱም ዜጎች በተለያየ ምክንያት የተወለዱበት ወይንም የሚኖርበትን ክልል በመተው ወደ ሌላ RealAudioMP3 የአገሪቱ ከተሞች የተዘዋወሩት እና በመዘዋወር ላይ የሚገኙት ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ተጋልጠው የሚገኙት ጉዳይ በማስመልከት፣ የአገሪቱ መንግሥት እነዚህ ተፈናቃይ እና ስደተኞች ወደ መጡበት ከተማ ተመልሰው ዳግም ኑሮአቸውን እንዲመሩ ካልሆነም ተሰደው በሚገኙበት በተስተናገዱበት ከተማ ቀርቦ መደገፍ እና ሕይወታቸውን ለመምራት የሚችሉበትን እንድል ለመፍጠር ያለመ አዲስ እቅድ መጠኑ በይፋ አስታውቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ የሚከታተለው የባላይ ድርገት በኢራቅ የአገር ውስጥ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ብዛት ከአንድ ሚሊዮን ከግማሽ በላይ ሲገምት የኢራቅ የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ ሚኒ. ቢሮ ከአንድ ሚሊይን በታች ናቸው ሲል፣ የኢራቃውያ የአገር ውስጥ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ብዛታ በተመለከተ በተባበሩት መንግሥታት የበላይ ድርገት እና የኢራቅ መንግሥት የሰጡት መገልጫ የተለያየ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ በሶሪያ እና በሊባኖስ በአጭር ጊዚ ውስጥ የኢራቅ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ በሶሪያ በሊባኖስ በዮርዳኖስ እና በግብጽ ያለው ሁኔታ በቅርብ ለመከታተል ሲባል የስደተኞች እና የተፈናቃዮች ጉዳይ የሚንከባከቡ ቢሮዎች እንደሚከፈቱ የኢራቅ መንግሥት መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.