2011-01-07 12:49:30

ብፁዕ አቡነ ስታሊያኖ፦ በዓለ ግልጸት እውነተኛ እና አዲስ የሰው ልጅ ሕይወት መግለጫ


በኢጣሊያ የኖቶ ከተማ ሊቀ ጳጳስ የነገረ መለኮት ሊቅ ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮ ስታሊያኖ ከበዓለ ልደት ቀጥሎ በኵላዊት ቤተ ክርስያን ስለ ተከበረው በዓለ ግልጸት ለእግዚእነ አስመልከተው በቫቲካን ረዲዮ ባቀረቡት አስተንትኖ እንዳመለከቱት፣ RealAudioMP3 በዓለ ግልጸት ለእግዚእነ የእግዚአብሔር ልጅ ሥጋ ለብሶ የተወለደበት እርሱም ግልጸት ማለት መሆኑ ሲታወቅ፣ የሰው ልጅ እውነተኛው እና አዲስ ሕይወት የተገለጠበት የተረጋገጠበት ዕለት ነው። ምክንያቱም በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት እውነተኛው እግዚአብሔር ለዓለም እራሱን ለየት ባለ መልኵ ገልጠዋል።

ሰብአ ሰገል፣ የከዋክብት ተመራማሪዎች የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናል እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። የሚለውን ቃለ ወንጌል በመጥቀስ፣ ሰብአ ሰገል የሰው ልጅ እውነተኛውን የሕይወት ትርጉም ፍለጋን የሚወክሉ ተግባር እና ሐሳብ መግለጫ ናቸው። የሰው ልጅ የሚያደርገው የሕይወት ትርጉም ፍለጋ እውነተኛ ከሆነ የትርጉሙ ማረፊያው እግዚአብሔር የሚሰዋ ፍቅር ለመሆን ሥጋ ለብሶ እርሱን እንመስል ዘንድ እኛን መስሎ፣ በጠቅላላ በሰው ታሪክ ዘንድ ተስፋ በመሆኑ የሰው መሆኑ ተካፋይ ከሆነው ጋር የሚያገናኝ ይሆናል። ጨለማን የሚያገል ብርሃን፣ የደካሞች የተናቁት በስቃይ እና በመከራ የሚገኙት የተነጠሉት ሰብአዊ ክብራቸው የተነፈጉትን መስሎ የዓለምን ጥበብ በእግዚአብሔር ሞኝነት እርሱም እውነተኛ ጥበብ ሆኖ መምጣቱን የተረዱት ሰብአ ሰገል እውነተኛ የሕይወት ትርጉም ፍላጎት ምረፊያ ፍጻሜ ማን መሆኑና የት እንደሚገኝ ያረጋገጡ ናቸው። የት እና ወደ ማን መሄድ እንዳለበን በትክክል መንገዱን ያመለከቱ የሰው ልጅ እውነተኛ መሻት ገላጮች ናቸው ብለዋል።

ሰብአ ሰገል የከዋክብት ተማራማሪዎች በቤተ ልሔም በረት ተገኝተው እዛው ያዩት ሕፃን እግዚአብሔር መሆኑ ለይተው በማወቅ በእርሱ ዘንድ ደምቆ የሚታየውን ውበት የሰው ልጅ ውበት መግለጫ መሆኑም ተገንዝበው ለእግዚአብሔርነቱ ሰገዱ የላቀው ክብር ያለውንም ገጸ በረከት አቀረቡለት። የነዚህ ተማራማሪዎች ሁኔታ በሥነ ምርምር እና በእምነት መካከል ምንም ዓይነት የተቃውሞ እና የመጻረር ባህርይ እንደሌለ የሚያረጋገጥ ትእምርት ነው። በፊደስ ኤት ራዚዮ እምነት እና ምርምር በሚል ርእስ ሥር ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ከደረሱት አዋዲ መልእክት ለመረዳት እንደምንችለውም፣ በእምነት እና በምርምር መካከል የተገባው አዲስ ቃል ኪዳን እርሱም በበዓለ ግልጸት ዘእግዚእነ ያለው እውነተኛው የታሪክ የእምነት ገጠመኝ ያረጋገጠው እውነት መሆኑ እንገነዘባለን። ስለዚህ ይህ የእግዚብሔር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የሰው ልጅ እወተኛው ስብእናው ተገልጠዋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.