2011-01-07 12:50:51

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ፣ ሕፃን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልክ መግለጫ ነው


ከትላትና በስትያ በበዓለ ግልጸት ለእግዚእነ ዋዜማ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሮማ በሚገኘው የሕክምና ማእከል አስጎስቲኖ ጀመሊን ዘንድ በመሄድ እዛው በሕፃናት የሕክምና መስጫ ክፍል ተገኝተው ሕሙማን ሕጻናት እና የዚህ የሕጻናት ማከሚያ ቤት የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ጋር ተገናኝተው ባሰሙት ንግግር፣ እግዚአብሔር እንደ ሕፃናት ሆኖ ሥጋችን ለብሶ ሲመጣ፣ ዘወትር ከሕፃናት RealAudioMP3 ጎን መሆኑ እና ለእያንዳንዳችን ማንኛውም ሕፃን የእርሱ መልክ መግለጫ መሆኖናቸውን ለማረጋገጥ ለመመስከር ለመግለጥ ነው ብለዋል።

ሰብአ ሰገል የተወለደውን እግዚአብሔር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት እርሱ ወደ ተወለደበት በረት የላቀ ክብር ያለው ገጸ በረከት በመያዝ እንደሄዱ በማመን፣ እኔም ይላሉ ቅዱስ አባታችን እንደ ሰብአ ሰገል ወደ እናንተ መጥቻለሁ። ለሕፃናቱ ያላቸውን ቅርበት ፍቅር እና አክብሮት ለመግለጥ ቅዱስነታቸውም ለሕጻናቱ የተለያዩ ገጸ በረከብት በማቅረብ፣ ሁሉም ለእነዚህ ሕፃናት እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠን ታላቅ እና እውነተኛው የማይጠፋው የማያረጀው ገጸ በረከብ በማቅረብ ፍቅር ይመሰክር ዘንድ አደራ ብለዋል።

የላቀው የእግዚአብሔር ፍቅር የተስተካከለ መግለጫ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በእርሱ አማካኝነት እግዚአብሔር ሥጋችን ለብሶ ወደ ምድር ወደ እኛ ሊመጣ ፈለገ፣ ልክ እንደ እናንተ ይላሉ ቅዱስነታቸው ሕፃን በመሆን ይኽ ደግሞ እግዚአብሔር ምንኛ እንደሚወደን መልካምነታችን እንደሚሻ ለመግለጥ ሲል ያሳየው ፍቅር በእናንተ ገጽ ታትሞ ይገኛል ብለዋል።

በሕክምና ላይ የሚገኙትን ሕፃናትን በመወከል አንዲት በጀርባ አጥንት ሰላላ በሚያደርግ ከባድ በመሽታ የተጥቃቸው ታዳጊ ወጣት ባሰማቸው ንግግር፣ ቅዱስነታቸው ሕፃናቱን ለመጎብኘት በመምጣታቸው አመስግና፣ ክርስቶስ ጋር መገናኘት ለሁሉም አስፈላጊ ነው። ሁላችን የተለየው የላቀውን ሥጦታ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቀርብለት ካለች በኋላ፣ ቅዱስ አባታችን በዚህ አቢይ በዓል ታማሚ ሕጻናት ጋር በመገናኘት ያሳዩት ፍቅር የእግዚአብሔር ጥበቃ ምስክር ነው እንዳለች የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

በጀመሊ ሆስፒታል የሕጻናት ክፍለ ሕክምና አስተባባሪ የሕክምና ሊቅ ክላውዲያ አረንደሊ ቅዱስ አባታችን ስላካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችን ከታማሚ ሕጻናት ከጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች የሕሙማን ሕጻናት ወላጆች ጋር በመገናኘት ያሳዩት አባታዊ ፍቅር በእውነቱ የጌታችን በዓለ ልደት በምናከብርበት እለት የታደልነው አቢይ ሥጦታ ነው። ለታማሚ ሕጻናት የሚያስፈልገው አባታዊ ፍቅር ፈገግታ እና ጥበቃ በትክክል ያሳዩ የሕፃናቱን ልብ ያዳመጡ እና ለሕፃናቱ ልቡ የተስተካከለ ተገቢ ቃል ያሰሙ ናቸው፣ የቅዱስ አባታችን በሕፃናት ማከሚያ ቤት መገኘት በእውነቱ በሕፃናቱ ላይ ደስት ፈገግታን አነቃቅተዋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.