2011-01-05 13:11:21

ብፁዕ ካርዲናል ኢቫን ዲያስ በቪየትናም


የአስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ኢቫን ዲያስ በቪየትናም የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ዓመተ ኢዮቤል ምክንያት በመካሄድ ላይ ያለው የሶስት ቀናት መንፈሳዊ ባህላዊ መርሃ ግብር መዝጊያ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ወክለው ትላትና በላ ቫንግ በሚገኘው ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ተገኝተው ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ መምራታቸው የቅድስት RealAudioMP3 መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በቪየትናም ዓመተ ኢዮቤል ምክንያት በመካሄድ ላይ ያለው የሶስት ቀናት መንፈሳዊ እና ባህላዊ መርሃ ግብር ነገ በበዓለ ግልጸት የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ በቪየትና ዳንግ ትሮንግ እና ዳንግ ንጎአይ በተቋቋመው መንበረ ሐዋርያዊ ወኪለ አማካኝነት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በዚያች አገር በመግባት ሐዋርያዊ አገልግሎት መስጠት እንደጀመረች ሲነገር፣ ይህ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በቪየትና የገባችበት እና ስብከተ ወንጌል ያነቃቃችበት 50ኛ ዓመት ምክንያት የተጀመረው የሶስት ቀናት መንፈሳዊ እና ባህላዊ ክብረ በዓል ቅዱስ አባታችንን የወከሉት የአስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካዲናል ዲያስ፣ በዚህ በላ ቫንግ በሚገኘው ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ተብሎ በሚጠራው በ18ኛው ክፍለ ዘመን በዚያኑ ክልል ክርስትና የተቀበሉት በወቅቱ የፈረንሳይ ቀኝ ገዢዎች ተባባሪ ናቸው በሚል ሰበብ ሥደት እና መከራ ላጋጠማቸው እና በላ ቫንግ ጫካ እርሃብ በሽታ እና ዘርፈ ብዙ ችግር ቢያጋጥማቸው በጋራ የመቅጸሪያ ጸሎት በማሳረግ ላይ እያሉ ሕፃን እየሱስ የታቀፈች ማርያም በሁለት መላእክት ታጅባ በመገለጥ ተስፋ እንዳይቆርጡ እናታዊ ከለላዋን እንደሰጠቻቸው የቤተ ክርስትያን የታሪክ ማኅደር የሚያረጋግጠው በዓል ይመራሉ። ይህ በላ ቫንግ የሚገኘው ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ እ.ኤ.አ. በ 1961 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ ወደ ማርያማዊ ባሲሊካ ክብር ከፍ እንዲ መወሰናቸው ይነገራል።

በአገሪቱ የኮሙኒዝም ሥርዓት ሥልጣን ላይ በነበረበት ዘመን ይህ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ እና ክልሉ በጠቅላላ ተወርሶ ሲያበቃ ሕዝቡ ግን ተስፋ ሳይቆርጥ ማርያማዊ መንፍሳዊነቱን በመቀጠል እ.ኤ.አ. በ 1998 ዓ.ም. አለ ፍርሃት የማርያም መገለጥ ሁለት መቶኛው ዝክረ ዓመት ምክንያት ሕዝቡ የአገሪቱ መንግሥት እና የጸጥታ ኃይሎችን በመጋፈጥ ወደ ቅዱስ ሥፍራው በመሄድ ለማርያም ያለውን አክብሮት አማካኝነት እምነቱን መመስከሩ የቤተ ክርስትያን ታሪክ ያወሳዋል።

ይህ በመንግሥት ተወርሶ የነበረው ቅዱስ ሥፍራ ባለፉት ዓመታት የአገሪቱ መንግሥት ለሁይ ሰበካ ማስረከቡ ሲገለጥ፣ የተለያዩ ከአገሪቱ ውጭ የሚገኙት የቨትናም ክርስትያን ምእመናን እና በአገር ውስጥ በሚገኙት በሰጡት እርዳታ አማካኝነት በዚያ ቅዱስ ሥፍራ ማርያማዊ ባሲሊካ ለመገንባት በዚህ የኢዮቤል ክብረ በዓል ምክንያት ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ፍጻሜ ብፅዕ ካርዲናል ዲያስ በቅዱስ አባታችን ስም የማርያማዊ ባሲሊክ የግንባታ መሠረተ ድንጋይ ማኖራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቪየትናም በ 2 ሺህ 200 ቁምስናዎች የሚተዳደሩ በ2 ሺሕ 900 ካህናት መንፈሳዊ እንክብካቤ የሚያገኙ በጠቅላላ ስምንት ሚሊዮን ካቶሊክ ምእመናን እንዳሉ ሲነገር፣ 10 ሺሕ ደናግል 1 ሺሕ 500 የዘርአ ክህነት ተማሪዎች እና 40 ሺሕ የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች እንዳሉ በቪየትናም የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የማስታወቂያና የሕዝብ ግኑኝነት ቢሮ ካሰራጨው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.