2011-01-05 13:16:40

በኢንዶነዢያ፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሰላም መልእክት አንድምታ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን 2011 ዓ.ም. በይፋ ያስተላለፉት ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት በኢንዶነዢያ ለአቢይ ተስፋ መሠረት መሆኑ በአገሪቱ በጃቫ ከተማ በሚገኘው የሰማራንግ ሰበካ የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ድርገት RealAudioMP3 ተጠሪ ኣባ አሎይስ ቡዲፑርኖሞ በግለጣቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የቅዱስ አባታችን የሰላም መልእክት እና የኢንዶነዢያ ሕገ መንግሥት መሠረታዊ አቋም በሚል ርእስ ሥር በተካሄደው ጥናት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሰላም መልእክት የኢንዶነዢያ ሕገ መንግሥት አምስት መሠረታዊ አቋሞች፣ እነርሱም እምነት፣ ሰብአዊ ቅንነት እና ፍትህ አንድነት፣ ዴሞክራሲ እና ማህበራዊ ፍትህ የተሰኙትን መመሪያዎቹን የሚያጎላ ከልዩነት የሚመነጨው አመክንዮ አዘል ውህደት የሚያነቃቃ እና የሚያብራራ ነው። በትክክል በዚህ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ዓለም አቀፋዊ የሰላም መልእክት ሥር የኢንዶነዢያ ሕገ መንግሥት መለየት እንድሚቻል አባ ቡዲፑርኖሞ ማብራራታቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት በመግለጥ፣ እ.ኤ.አ ከ 1945 ዓ.ም. ወዲህ ፓንካሲላ በመባል የሚጠራው የኢንዶነዢያ አገራዊ ፍልስፍና የአገሪቱ እና የሕዝቧ ሕይወት መግለጫ እና መመሪያ የሆነው መሠረታዊ ሐሳብ ለመለየት የሚቻልበት ዓለም አቀፋዊ የሰላም መልእክት መሆኑ በሁሉም የታመነበት እውነት ነው እንዳሉ የዜናው አገልግሎት አክሎ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.