2011-01-05 13:14:17

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፦ ጋውዲዩም ኤት ስፐስ-ደስታ እና ተስፋ


በቫቲካን ረዲዮ ኢየሱሳዊ ካህን አባ ዳሪዩስ ኮዋልቺዝክ ዘወትር ማክሰኞች በጣልያንኛ ቋንቋ ስለ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የማይሻሩ ውሳኔዎች በማስደገፍ የጀመሩት የሥርጭት መርሃ ግብር በመቀጠል ትላንትና በቫቲካን ሁለትኛው ጉባኤ RealAudioMP3 ሰነድ ዘንድ ሰፍረው ካሉት ውሳኔዎች እርሱም ጋውዲዩም ኤት ስፐስ - ሐሴተ እና ተስፋ የተሰኘው በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ውሳኔ ዘንድ ተቀምጦ ያለው ኅላዌ ቤተ ክርስትያን በወቅታዊው ዓለም የሚተነትን የውሳኔ ሰነድ መሆኑ አስታውሰው፣ ቤተ ክርስትያን የሰው ዘር ቤተሰብ አገልጋይ መሆኗ የተሠመረበት የቤተሰብ ተቋማዊ ገጽታው እና መሠረቱን የሚያናጋ ላደጋ የሚያጋልጠውን ቀደም ብሎ ያወቀ ነቢያዊ ባህርይ ያለው መሆኑ በማብራራት፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በዚህ ጋውዲዩም ኤት ስፐስ - ሐሴት እና ተስፋ በተሰኘው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ውሳኔው አማካኝነት የቤተ ክርስትያን ኅላዌ እና ተግባር በወቅታዊው ዓለም የሚያረጋግጥ፣ የሚለይ በቤተ ክርስትያን እና በኅብረተሰብ ዘንድ ያለው ግኑኝነት በቅድሚያ ቤተሰብ የሰው ልጅ፣ የኅብረተሰብ እና የክርስትያን ማኅበረ - ሰብ ሃብት መሆኑ በማብራራት፣ በቃል ኪዳናዊ ውህደት (በሚሥጢረ ተክሊል የጸና) እና ከቤተሰብ ደስታ ጋር የተቆራኘ ማኅበራዊ ሃብት ነው የሚለው ጥልቅ ሓሳብ በስፋት የሚያብራራ ነው።

በአሁኑ ወቅት በቤተ ክርስትያን የሚታዩት ችግሮች ዙሪያ ብዙ ውይይት ይደረጋል፣ ይህ ጥያቄ ደግሞ የካህን ሕይወት መሠረት ያደረገ ብቻ ሆኖ ሲቀርብ ይታያል፣ በርግጥ የአገልጋዮች ማለትም የካህናት ባህርይ ሁኔታ እና ጥራት በማኅበረ ክርስትያን ጥራት ላይ ተጽእኖ አለው፣ እውነትም ነው፣ ነገር ግን የቤተ ክርስትያን ችግር የካቶሊክ ቤተሰብ ቀውስ የሚያስከትለው ወይንም ነጸብራቅ ነው። ካቶሊክ ቤተሰብ የቤተ ክርስትያን እና የካህናት ሁኔታ መግለጫ ነው። ስለዚህ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የካቶሊክ ቤተሰብ መዳከም መዛል ጉዳይ በማስደገፍ የዛሬ 45 ዓመት በፊት የሰጠው ትንተና ወቅታዊነት ያለው ነው። ጋውዲዩም ኤት ስፐስ በተሰኘው የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ውሳኔ ዘንድ የቤተሰብ ተቋማዊ ሐቅነቱ ነጻ ፍቅር እየተባለ ዓለም በሚሰብከው ፍቅር ባልሆነ የፍቅር አገላለጥ እና አኗኗር ፍቅር ያለው ኃላፊነት የሚደልዝ የሚያረጋግጠው የፍች ምርጫ እኔ ባይነት፣ ጸረ ሕይወት በሆነው የሞት ባህል አማካኝነት ወሊድ ለመቆጣጠር ሚደረገው ጥረት እና በኤኮኖሚ ችግር ለአደጋ ተጋልጦ እንደሚገኝ በቁጥር 47 የሰጠው ማብራሪያ በግልጽ የሚታይ ነው።

የእግዚአብሔር አገልጋይ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ Novo millennio ineunte - የአዲስ ሚለኒዩም ጅማሬ በሚል ርእስ ሥር በደረስዋት ሓዋርያዊ ምዕዳን ዘንድ “ምንም’ኳ በእጅግ አንሰራፍቶ እና ተስፋፍቶ ብዙሃን ተከታዮች እና አራማጆች ያሉት ተጽእኖ ያለ ቢሆንም፣ ቤተ ክርስትያን ለማንኛውም ዓይነት ተጽእኖ እጅዋን አትሰጥም” ያሉትን ሐሳብ በማስታወስ፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሁሉም ክርስትያን ለቤተሰብ ድጋፍ ይተጋ ዘንድ ጥሪ ያቀርባል፣ በጋውዲዩም ኤት ስፐስ ቁጥር 52 “የቃል ምሥክርነት መልካም ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ጋር የሚግባባ የሕይወት ምሥክርነት ያቀርብ ዘንድ ያሳስባል፣ ቤተ ክርስትያን በጥበብ ለሚሰጣቸው ጥሪ ተግተው የሚጣጣም የሚስማማ የተወሃደ መልስ ለመስጠት የሚተጉ ወንዶች እና ሴቶች ያስፈልጉዋታል። ቤተሰብ የተለያዩ ሃይማኖቶች ለሚደረጉት የጋርው ውይይት ተቀዳሚ አስተያየት መሆን አለበት ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.