2011-01-03 16:17:57

ኩባ፣ ብፁዕ ካርዲናል ኦርተጋ


እ.ኤ.አ. በ 2003 ዓ.ም. በኵባ የሰሜን አመሪካ ቅጥረኞች ናቸው በሚል ወንጀል በቁጥትር ሥር እንዲውሉ ከተደረጉት በቅርቡ 41 እሥረኞች መለቀቃቸው የሚዘከር ሲሆን ሌሎች ገና በእሥር የሚገኙት አስራ አንድ የፖለቲካ RealAudioMP3 እስረኞች በሚቀጥሉት ወራት ነጻ ይለቀቃሉ የሚል ተስፋ እንዳለ የኩባ ርእሰ ከተማ ሃቫና ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ኻይመ ኦርተጋ ለዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ምክንያት ሃቫና በሚገኘው ካቴድራል መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት በመግለጥ፣ የኵባ መንግሥት እስረኞቹ ነጻ ይለቀቃሉ በማለት ያሰራጨው የተስፋ ዜና ግልጽ እና ይፋዊ ነው እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።

የዛሬ ስድስት ወር በፊት ብፁዕ ካርዲናል ኦርተጋ ከርእሰ ብሔር ራውል ካውትሮ ጋር በመገናኘት ባካሄዱት የውይይት ፍጻሜ 52 የፖለቲካ እስረኞች ነጻ ይለቀቃሉ በማለት መግለጫ ሰጥተው እንደነበር የሚዘከር ሲሆን፣ ከተባለው ቁጥር ብዛት ውስጥ 41 ከእስር ነጻ ተለቀው 40ዎቹ ወደ ስፐይን መሄዳቸው እና አንዱ ብቻ በአገሩ ለመቅረት መምረጡንም የሚዘከር ሲሆን፣ የተቀሩት 11 ነጻ የተለቀቁ ከሆነ በአገራቸው ለመቅረት እንደሚሹ ቀድም በማድረግ ማሳውቀቸው ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.