2011-01-03 16:16:29

ናይጀሪያ


በናይጀሪያ የፕላተእው ግዛት ርእሰ ከተማ ጆስ ባለፉት ቀናት ከከተማይቱ ወጣ ብሎ በሚገኘው ክፍለ ከተማ ክልል በተጣለው ጥቃት ሳቢያ ሰባት ሰዎች የሞት አደጋ እንደደረስባቸው እና ሌሎች ቁጥራቸው ገና በውኑ ያልታወቀ የመቁሰል RealAudioMP3 አደጋ እንደደረሰባቸው ሚስና የዜና አገልግሎት አመለከተ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ውጥረት እና የሞት ጥቃት በስፋት የሚታይበት የጆም ከተማ ከናይጀሪያ ርእሰ ከተማ በስተ ደቡብር 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ክልል በእንስሳት ርቢ የሚተዳደሩት የፉላን ዘላኖች አባላት ውስጥ የእንስሳት ሃብት ለማካበት በማቀድ በተለያዩ ሶሶት መንደሮች ላይ ጥቃት መጣላቸው የዜናው አገልግሎት በመጥቀስ፣ በናይጀሪያ የአፍሪቃ ወንጌላውያን ልኡካን ማኅበር አለቃ አባ ማውሪስ ሄንርይ ይህ በፉላን ዘላኖች የኅበረተሰብ ክፍል የተጣለው ጥቃት ሃይማኖታዊ ምክንያት ያለው ሳይሆን ኤክኖሚያዊ አድማስ ያለው ነው ካሉ በኋላ፣ በአሁኑ ወቅት የታየው ውጥረት ተገን በማድረግ የተለይዩ ዓላማ ያላቸው የወንጀል ቡድኖች ጥቃት እያስከተሉ ናቸው። ስለዚህ የአገሪቱ የጸጥታ ኃይሎች የሕዝብ ደህንነት እና ጸጥታ በተለይ ደግሞ በገጠሩ ክልል ጸጥታ እና ሰላም ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል እንዳሉ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.