2010-12-27 14:39:12

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ ኣስተምህሮ (26/12/2010)


ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደተ ቀጥሎ ያለው እሁድ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን በሊጡርጊያዊ ባሕረ ሀሳብ መሠረት የቅድስት ቤተሰብ በዓል እንደምታከብር የሚታወቅ ሲሆን፣ ትላትና እሁድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ይኸንን አቢይ የቅድስት ቤተሰብ በዓል ምክንያት እኩለ ቀን በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ከኢጣሊያ እና ከውጭ አገር የመጡ ምእመናን በቅዱስ ጴጥሮስ RealAudioMP3 አደባባይ በተገኙበት ጸሎተ መልእከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ባቀረቡት አስተምህሮ፣ የሚያጋጥመንን ፈተና እና ሥጋት የሕይወት አብነት የሆነቸውን ቅድስት ቤተሰብ አብነት በመከተል በፍቅር በመጋፈጥ እንድናሸንፍ አሳስበዋል።

የሚወለደው ሕፃን የግዚአብሔር ሚሥጢር ይዞ የሚመጣ ለቤተሰብ ከግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋ እና አቢይ ተአምር ነው። ይኸንንም ወላጆች በቅርብ ጠንቅቀው የሚያውቁት እውነት ነው። ስለዚህ ወደ ዓለም የሚመጣው የሚወለደው ሕፃን አስፈላጊ ከመሆኑም ባሻገር በቤተሰብ ዘንድ ተገቢ መስተንግዶ ያስፈልገዋል፣ ውጫዊው ሽርጉድ እጅግ አስፈላጊ አይደለም፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በበረት ውስጥ ነው የተወለደው፣ ሆኖም ግን ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም እና ከቅዱስ ዮሴፍ ከቀረበለት ፍቅር የመነጨ መስተንግዶ በመፈቀር ዘንድ ያለው ለእነርሱ ደህንነት የሚያሰጠው ዕለት በዕለት ባደገ ቁጥር የሕይወት ትርጉም እንዲገነዘቡ የሚያደርገው ውበት እና ርኅራሄ እንዲያጣጥም አድርጎታል ብለዋል።

በመጨረሻም መላ ቤተሰብ በሚያጋጥመው ፈተና እና ችግር ሳይሰናከሉ በሚሥጢረ ተክሊል መሠረት አንድነት የሚፈጥሩት ባለ ትዳሮች ዘወትር ተግተው ፍቅርን እንዲንከባከቡ እና እንዲያጎለብቱ በእማኝነት የሕይወትን እና የሕንጸት አብነት ይሆኑ ዘንድ ለቅድስት ድንግል ማርያም እና ለቅዱስ ዮሴፍ ጥበቃ በማቅረብ አክለውም በዚህ አቢይ በዓል ምክንያት በተለያዩ ክልል የአመጽ ሰለባ የሆኑትን በማሰብ የጥላቻ እና የቂም በቀል መንፈስ ከሥር መሠረቱ ጨርሶ እንዲወገድ ጥሪ በማቅረብ፣ ለመላው ኅብረሰብ ደህንነት እና መረጋገት በማሰብ ግጭቶች እና ውጥረቶች በጠቅላላ በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲያገኙ አደራ በማለት፣ በቅድስት ቤተሰብ በዓል ሄሮዶስ በምድረ ግብፅ የፈጸመው እልቂት በቅርብ ተመኩሮ ያላት ቅድስት ቤተሰብን ስናከብር በጦርነት በዓመጽ እና ካለ መከባበር ቤት እና ንብረታቸውን ጥለው ለሚሰደዱት እናሰብ ብለው፣ ሁሉም ምእመናን ተስፋ እርቅ እና ሰላም እንዲረጋገጥ እግዚአብሔር የሰዎችን ልብ እንዲነካ በማሰብ በሚያቀርቡት ጸሎት እንዲተባበሩዋቸው አደራ በማለት ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር አሳርገው ለሁሉም መልካም የቅድስት ቤተሰብ በዓል ተመኝተው ቡራኬ ሰጥተው ምእመናንን አሰናብተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.