2010-12-27 14:41:16

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ፦ የሚሰዋ ፍቅር ብቻ ነው ዓለምን የሚለውጠው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከተለያዩ በእናቴ ብፅእት ተረዛ የፍቅር ደናግል ማኅበር ሥር ከሚረዱት ውስጥ ለተወጣጡት ለ 250 ድኾች ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ የተለያዩ ገዳማውያን ደናግል እና ካህነት የተሳተፉበት ባቀረቡት የምሳ መስተንግዶ ተገኝተው አብረው ማእድ በመካፈል ባቀረቡት አስተምህሮ፣ ዓለም የሚለውጠው እውነተኛው ኃይል የሚሰዋ ፍቅር RealAudioMP3 ብቻ ነው በማለት፣ እግዚአብሔር ምንኛ እንደሚያፈቅረን ለመግለጥ ለእያንዳንዳችን ቅርብ መሆኑንም ለማረጋገጥ ሥጋችን ለብሶ እንደኛ ሰው ሆኖ በበረት ውስጥ መወለዱን አስታውሰው፣ ይኽ ደግሞ ክፋትን እንድናሸንፍ እና ከኃጢአት ነጻ እንዲያወጣን ተስፋን እንዲሰጠን ብቻችን እንዳልሆንም አረጋግጦልናል።

በዚህ ካለ ምንም ልዩነት እጅግ በድኽነት ለተጠቁት ለተገለሉት የኅብረተሰብ ክፍል በሚሰዋ ፍቅር በማገልገል የእግዚብሔር ብሩህ አባታዊ ጥበቃ እና መልካምነቱን አሳቢነቱን የመሠከሩ በእያንዳንዱ በተናቀው እና በጠና ድኽነት ሥር ያለው ሰው ዘንድ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምስል በመለየት በማፍቀር ያገለገሉት እናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘ ካልኩታን አስታውሰው፣ ለማፍቀር እና በእግዚአብሔር ፍቅር ለማፍቀር በትህትና እዩልኝ ስሙልኝ ሳይሉ ለእኔ የላቀው ስጦታ ኢየሱስ ክርስቶስን ማፍቀር እና በድኾች ዘንድ እርሱን ማገልገል ነው በማለት የኖሩት ሕይወት አስታውሰው፣ የሰው ልጅ መሠረት የሌለው በውጫዊ ደስታ ፍለጋ በተጠመደበት ዓለም የእናቴ ብፅዕት ተረዛ የፍቅር ደናግል ማኅበር ለሌሎች የሚል ይኽ ዓለም የሚያቀርበው እኔነት ማእከል የሚያደርግ የልቅ ራስ ወዳድነት አመክንዮ የሚከተለው መንገድ ፍቅር የሚያስወግደውን የእግዚአብሔር ነጻው ፍቅር የሚመሰክሩት እና የሚኖሩት የሚሰዋው ፍቅር የሚያፈቅር ሕይወት እውነተኛ ደስታ የት እንዳላ እና የት እንደሚገኝ የሚያረጋግጥልን ነው ብለዋል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለ የቅድስት መንበር የዜና እና የኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የተካሄደው የምሳ ግብዣ አስመልክተው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አባታችን የምሣ ግብዣ ናዘጋጁበት በጳውሎስ ስድስተኛ አደራሽ እንደደረሱ በብፅዕት እናቴ ተረዛ የፍቅር ደናግል ማኅበር ጠቅላይ አለቃ እናቴ መሪ ፕረማ እና በፍቅር ወንድሞች ማኅበር ጠቅላይ አለቃ ኣባ ሰባስቲያን እና የእናቴ ብፅዕት ተረዛ መናንያን ማኅበር አለቃ ወንድም ብራይን እንዲሁ በጠቅላላ በምሣው ግብዣ ተሳታፍያንን በወከሉት አቀባበል እንደተደረገላቸው ሲታወቅ፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት የሚያወሱ መዝሙሮች በእናቴ ብፅዕት ተረዛ የፍቀር ማኅበረ ዘማርያን ብድን አማካኝነት እንደቀረበም ለማወቅ ሲቻል፣ የደስታ ስሜት የጎላበት አጋጣሚ እንደነበረ አባ ሎምባርዲ በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.