2010-12-24 14:25:10

ር.ሊ.ጳ. በቢቢሲ ሬድዮ የልደት መልእክት ኣስተላለፉ


ለዕለቱ የሚሆን አስተንትኖ “Thought for the day” በሚለው የትልቅዋ ብሪተይን ሬድዮ ስርጭት ቢቢሲ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ለመጀመርያ ግዜ የልደት መልእክት ኣስተላልፈዋል። የዚሁ ዛሬ ጥዋት በትልቅ ብሪጣንያ ሰዓት አቆጣጠር በጥዋቱ 7 ሰዓት ከ45 ደቂቃ የተላለፈው መልእክት ይዘት እንደሚከተል ነው። ባለፈው መስከረም በተባበሩት የታላቅ ብሪጣንያ መንግሥት ያደረግሁትን የአራት ቀና ጉብኝት በትልቅ ኣድናቆት ሳስታውስ እንደገና ሰላምታየን ለማቅረብ ዕድል በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ። እንዲሁም በዚሁ የክርስቶስ በዓለ ልደትን ለማክበር በምንዘጋጅበት ግዜ በመላው ዓለም ለሚገኙ የዚህ ፕርግራም ኣድማጮች ሰላምታየን ኣቀርባለሁ። በዚህ ምርጥ ግዜ ኅሊናችን በእግዚአብሔር የተመረጠው ሕዝብ ማለትም የእስራኤል ልጆች በትልቅ መጠባበቅ የነበሩበትን ግዜ ታሪክ በማስታወስ ወደ ኋላ ይጓዛል። . እግዚአብሔር እንዲልክላቸው ቃል የገባላቸውን መሲህ ይጠባበቁ ነበር፣ በኅሊናቸውም ከውጭ ኣገር ሰዎች ጭቆና በማላቀቅ ነፃነታቸውን የሚያስመልስ ትልቅ መሪ ይጠባበቁ ነበር።

እግዚአብሔር ሁል ግዜ ለሰጠው ተስፋ ታማኝ ነው ሆኖም ግን ዘወትር በድንገትና ባላሰብነው በሚያስደንቅ ሁኔታ የሰጠውን ተስፋ የሚፈጽም ኣምልክ ነው። በእርግጥ በቤተልሔ የተወለደው ሕፃን ነፃነትን ኣመጣ ሆኖም ግን በቦታውና በግዜው ለነበሩት ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለሁል ግዜ ለመላው ዓለም ሕዝብ የሚሆን መድኃኒት ሆነዋል። ይህ ነፃነት በወታደራዊ ዓመጽ እንደተገኘ ፖሎቲካዊ ነፃነት ኣልነበረም፣ ክርስቶስ ሞትን ለኣንዴን ለመጨረሻ ደመሰሰው በኣሰቃቂ ሁኔታ በመስቀላይ ላይ ተቸንክሮ በመሞትም ሕይወት ሰጠን። የሰው ልጅ ሥልጣንና ሃብትን ከሚያሳዩ መሀል ኣገሮች ርቆ በድህነትና በጨለማ ተውልደ፣ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ለእኛ ፍቅር ሲል ሰብአዊ ባህርይ ለበሰ፣ እንደ ሰው ልጅ ድካማችንና በቀላሉ ተጐጂ መሆንን በመልበስ ጉዳት የሕይወት ጐዳናን ከፈተልን በዚህም ሕይወትን ኣትረፍርፎ ስለሰጠን ከእግዚአብሔር ጋር ሕይወትን እንድንካፈል ኣደረገን። በዚሁ በዓለ ልደት ይህን ምሥጢር በምናሰላስልበት ግዜ እግዚአብሔር ባሳየን ርኅራሄ ምስጋና እናቅርብለት፣ በኣከባቢያችን ላሉት ሁሉ ደግሞ እግዚአብሔር ጫና ከሚያደርግልን ሁሉ ነፃ በማውጣት ተስፋ እንደሚሰጠንና ወደ ሕይወት እንደሚጠራን በደስታ እንስበክ።

ውድ የእስኮትላንድ የእንግሊዝ ኣገርና የወይልስ እንዲሁም በሁሉም የዓለም ዳርቻ የምትገኙ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በዚሁ ቅዱስ ዘመን ሁላችሁንም በጸሎቴ እንደማስባችሁ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፣ ለቤተ ሰቦቻችሁ ለልጆቻችሁ ለታመሙ ወገኖች እንዲሁም በዚች ግዜ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ስለሚገኙ እጸልያለሁ።. በተልይም ስለሽማገሌዎችና የዚህ ዓለም ሕይወታቸውን በመፈጸም ስለሚገኙ እጸልያለሁ። የዓለም ብርሃን የሆነውን ክርስቶስ በሕይወታችሁ ውስጥ ያለውን የሆነ ጨለማ እንዲያወግድላችሁና ለእያንዳንዳችሁ ሰላምና ደስታ የሞላበት ልደት የማክበር ጸጋ እንዲሰጣችሁ እመኛለሁ፣ ሁላችሁንም እግዚአብሔር ይባርካችሁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.