2010-12-24 14:28:33

ሢመት


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ የኮስታድ ጳጳስ የነበሩ ብፁዕ ኣቡነ ዊልያም ስላተሪ የፕረቶርያ መትሮፖሊታ ሊቀ ጳጳስና የደቡብ ኣፍሪቃ ወታደራዊ ኣበነፍሶች ጳጳስ እንደሾሙዋቸው ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና ኣመልክተዋል። እንዲሁም የኪምበርልይ ጳጳስ የነበሩ ብፁዕ ኣቡነ ኣበል ጋቡዛን የመንበረ ሊቀ ጵጵስናው ሐዋርያዊ ኣስተዳዳሪ እንዲሁ እንድሾሙዋቸው ዜናው ኣያይዞ ጠቍመዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዱስነታቸው ጥቀ ክቡር ኣባ ሆን ታይ ፋይ የሚባሉ በሆንግ ኮንግ ዘርአ ክህነት የንባበ መለኮት ኣስተማሪ የነበሩ የሳለስያን ማኅበር ኣባል የኣሕዛብ ስብከተ ወንጌል ማኅበር ፕሮፓጋንዳ ፊደ ዋና ጸሓፊ እንዲሆኑ መሾማቸው ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.