2010-12-22 14:53:35

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተምህሮ (22.12.2010):


ከሚክያስ ትንቢት 5፣2-5 ‘ኣንቺ ግን ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ’ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሽዋ ብትሆኚም፣ አመጣጡ ከጥንት ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣ የእስራኤል ግዥ ከአንቺ የጣልኛል። ስለዚህ ወላዲቱ ኣምጣ እስክትገላገል ድረስ እስራኤል ትተዋለች፣ የተቀሩት ወንድሞቹም ተመልሰው ከእስራኤላውያን ጋር ይቀላቀላሉ። በእግዚአብሔር ኃይል በኣምላኩ በእግዚአብሔር ስም ታላቅነት ጸንቶ ይቆማል፣ መንጋውንም ይጠብቃል። በዚያን ግዜ ኃይልነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ ተደላድለው ይኖራሉ። እርሱም ሰላማቸው ይሆናል።’

ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፣ በዚሁ ከበዓለ ልደት ባሉ ቀናት ቤተ ክርስትያን ስለ ክርስቶስ ልደት እንድናስተነትንና የክርስቶስ በመሀከላችን መገኘት ሥጦታዎች እንድንቀበል ጥሪ ታቀርብናለች፣ የክርስቶስ መሀከላችን መገኘት ትልቁ ሥጦታ የሰው ልጅ ሁሉ ጥልቅ ተስፋንና መጠባበቅን እውን በማድረጉ ነው። የእመቤታችን ድንግል ማርያምና ቅዱስ ዮሴፍ እንዲሁም ጌታ በተወለደበት ግዜ የተቀበሉት ሰዎች ልብ የሞላው ደስታን እንካፈላለን። ይህ ጌታ ኣማኑኤል ነው፣ ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው። ከዚህ የበለጠ ሥጦታ የለም። ይህንን ያደረገው ደግሞ ከሥጋችን ሥጋ በመልበስ ከአባቶቻችን ኃጢኣት ነፃ ኣወጣን። ጌታ ከእኛ የሚፈልገው እንደእርሱ እንድንሆን፣ ዓለምን በእርሱ ዓይን ለማየት እንድንችል፣ ልባችን በእርሱ መጨረሻ የሌለው በጎነትና ምሕረት እንዲለወጥና እንዲታደስ ይፈልጋል።

በዚሁ በዓለ ልደት ኢየሱስ ሕፃን እያንዳንዳችን የሚመጣውን ጌታ ለመቀበል በመንፈስ የተዘጋጅን ሆነን እንዲያገኘን መልካም ምኞቴን እገልጣለሁ። እያንዳንዱ ቤተ ሰብ በዚሁ ቀናት በየቤቶቻችን የምንሠራው የልደት ማስታወሻ ግርግም እኛ ለመዳን የሚመጣውን ጌታ የመጠባበቅ መልካም ምልክት ነው። ይህ ግርግም በሕፃናት ላይ የሚፈጥረው ኣድናቆትና ደስታ በጌታ ምሥጢር ለተገለጠልን ፍቅር እንዲያቀርበን በድጋሚ መልካም ምኞቴን እገልጣለሁ። እመቤታችን ድንግል ማርያምንና ቅዱስ ዮሴፍን ይህንን ትልቅ ምሥጢር በታደሰ ደስታን ምሥጋና እንድናስተነትን እንዲረዱን እንጠይቃቸው።







All the contents on this site are copyrighted ©.