2010-12-21 15:35:27

የዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መንፈሳዊ ልጆች ማኅበር


የዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መንፈሳዊ ልጆች ማኅበር በሚል ስም የሚታወቀው መንፈሳዊ ንቅናቄ ዛሬ ከቀትር በኋላ በመላእክት ማርያም ቤተ ክርስትያን የልደት መዘጋጃ መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ። መሥዋዕተ ቅዳሴውን የሚያሳርጉ የማኅበሩ ኣበ ነፍስ ብፁዕ ኣቡነ ጃንጁልዮ ራዲቮ ናቸው።

የማኅበሩ መሥራች እናቴ ማርያሮዛ ሎ ፕሮቶ ስለ ማኅበሩ ኣላማና ስለሚያደርጉት መንፈሳዊ ተግባራት ሲገልፁ፣ ማኅበሩ በዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሥር የተመሠረተና ለጸሎት ለሱባኤ በየግዜው ስብሰባ እንደሚያካሄድ ብፁዕ ካርዲናል ካሚሎ ርዊኒ የደርሰላቸው ጸሎት እንደሚደግሙ፣ በተለይ የዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ብፅዕና እንዲከናወን እንደሚጸልዩ በዚሁ ኣዲስ ዓመት ቅዱስነታቸው በነዲክቶስ 16ኛ መልካም ዜና ቢያሰሙን እንዴት ደስ ባለን ነበር ስትል ምኞትዋን ገለጠች።

ስመ ጥር ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ማኅበሩን ሲመሥርቱ እንዳሉን ኣሁንም ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ እንደሚመሩን ኣዲስ የክርስትናና የእምነት ሕይወት ለማወጅ እንፈልጋለን፣ ከሙታን ተለይቶ የተንሣውን ክርስቶስ ለመመስከር ተነሥተናል፣ ኣሁን ደግሞ በቅርቡ ልናከበረው በመዘጋጀት ላይ ላለነው ልደት፣ ለእኛ ፍቅር ይህንን ታላቅ ምሥጢር በፈጸመ ኣምላክ ፊት ወላዋይ ሆነን ለመቅረት ኣንፈልግም። በዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መንፈስ የምንመራ መንፈሳውያን ልጆች ማኅበር ከ900 ኣባላት ነን፣ በሮም ቤተ ሰባት ቡድኖች ኣሉን፣ በየቊምስናው ማኅበሩን ልናቋቋም እየጣርን ነው፣ በሌሎች ኣገሮችም እንገኛለን። በየቊምስናው ማኅበር በማቆም የጸሎትና የመታደስ መንፈስ እንዲያሳድሩ ምእመናንን ኣደራ እንላለን፣ በሚጸለይበት ቦታ ሁሉ የእግዚአብሔር ቡራኬ ስላለ በጸሎት እንበርታ ሲሉ ማኅበሩ ለብዙ ሰዎች በረከትና ጸጋ እንዳስገኘ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.