2010-12-21 15:37:08

የኣፍሪቃ ካቶሊካውያን ወጣቶች በየኣገራቸው የሰላም የዕርቅ መልእክተኞች ለመሆን ይፈልጋሉ


ባለፉት ቀናት የመሃከለኛው ኣፍሪቃ ጉባኤ ጳጳሳት ዞን በየዓመቱ ‘የዞኑ የወጣቶች ቀኖች’ በማለት የሚያዘጋጁት የወጣቶች ስብሰባ፣ ‘ወጣቶች የፍትሕ የምሕረትና የዕርቅ ምስክሮችና ተግባሪዎች’ በሚል ርእስ በደምክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ዋና ከተማ ኪንሻሻ ተካሄደ። ኣምና በብሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ ተካሂዶ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ፊደስ የተባለ የዜና ኣገልግሎት ከቦታው እንደዘገበው፣ በጉባኤው 15 የካቶሊካውያን ወጣቶች እንቅስቃሴ ማኅበራት ከርዋንዳ ከብሩንዲ እና ከደሞክራስያዊት ሪፓብሊክ ኮንጎ ተሳትፈዋል።

ጉባኤው ለዞኑ ወጣቶች የሚሆኑ የተለያዩ የሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ሥራዎች ከማከናወን ባሻገር ለመላው ኣፍሪቃ ካቶሊካውያን ወጣቶች የሚሆን መርሓ ግብር ለመንደፍም ነበር የተሰበሰበው። ካስተላለፍዋቸው ውሳኔዎች መሃከል የዞኑ ወጣቶች በየሁለት ዓመት በዓለም ኣቀፍ ደረጃ ከር.ሊ.ጳ ጋር በሚደረገው የወጣቶች ቀን መንጽር ጉባኤ እንዲያካሄዱ፣ የመሃከለኛ ኣፍሪቃ ጉባኤ ጳጳሳት ማኅበር ኣባላት የሆኑ ጳጳሳትን በመጠየቅ በየቦታው ተከታታይ ሥልጠና *ፐርማነንት ፎርመይሽን እንዲካሄድ፣ በተለይ ደግሞ መላው የኣፍሪቃ ካቶሊካውያን ወጣቶች መሠረታዊ ሰብአዊና ክርስትያናዊ ዕሴቶች ላይ የተመሠረተ ሥልጠና ኣግኝተው ሥራ ኣጥነት ሙስና በዝምድና ኣሠራር የመሰሉትን ኣፍሪቃን እያንገላቱ ያሉት መጥፎ ነገሮች ከየኣገራቸው ለማጥፋት እንዲታገሉ ወስነዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.