2010-12-17 07:42:19

የጓዳሉፐ እመቤታችን ማርያም ክብረ በዓል


የደቡብ ኣመሪካ ጠበቃ የሆነችው የጓዳሉፐ እመቤታችን ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል ትናንትና በታላቅ ድምቀት እንደተከበረ ከቦታው የደረሰ ዜና ኣመልክተዋል።

ቅዱስነታቸው ትናንትና በመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ ኣስተምህሮ እንዳስታወሱት በዓሉ በተለይ ለመክሲኮ ባጠቃላይ ደግሞ ለደቡብ ኣመሪካ ሕዝብ ታላቅ የጸጋና የቅድስና በዓለ ነው። በየዓመቱ ከሃያ ሚልዮን ሕዝብ በላይ በቦታው በመገኘት መንፈሳዊ ንግደቱን ይፈጽማል።

የዚህ በዓል መሠረት እግዚአብሔር በመንፈስ ትሑታንንና ገሮችን መርጦ እንዴት በቀላል መንገድ ሊገለጥና የሰውን ልብ ለእምነትና ለንስሐ ሊለውጥ እንደሚችል የሚያመልክት እጅግ ኣስደናቂ ታሪክ ነው።

በ16ኛው ክፍለ ዘመን ኣዲሱ ዓለም ተብሎ ይጠራ በነበረው የደቡብ ኣመሪካ ክፍል ለስብከተ ወንጌል የተላኩ የቦታው ነዋሪዎችን ወንጌል ሲያበስሩና የተቀበልዋቸውን ጥቂት ትምህርተ ክርስቶስ ያስተምሩ ነበር።
የተኣምሩ መልእክተኛ የሆነው ኣዝተክ ከሚባሉ ህንዳውያን ኩዋህትላቶኣዚን የሚባል ሰውየ ናቸው፣ የስሙ ትርጉም በኣዝተክ ቋንቋ ‘እንደ ንስር የሚናገር’ ማለት ነው። በ1474 ዓም ተወልዶኣል፣ ለዓቅመ ኣዳም በደረሰ ግዜ ማሊትዚን የምትባል ሚስት ኣግብቶ በተክስኮኮ ሓይቅ ኣከባቢ ከኣጎቱ ጋር ይኖር ነበር። ሰባካነ ወንጌል በኣከባቢው በደረሱበት ግዜ በኣባ ቶሪቢኦ የሚባል ሰባኬ ወንጌል ከተጠመቁት ጥቂቶች ክርስትያኖች እነኚህ የጠቅስናቸው ሶስት ሰዎች ነበሩ፣ በ1525 ጥምቀት ተቀብለው ለእርሱና ለባለቤቱ ኽዋን ዲየጎ እና ማርያ ሉችያ የሚል የጥምቀት ስም ሲሰጣቸው ለኣጎቱ ደግሞ ኽዋን በርናርዲኖ የሚል የጥምቀት ስም ተሰጠው። የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ባለቤቱ ገና ልጅ ሳይወልዱ በ1529 ዓም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።

ኽዋን ድየጎ በ55 ዓመቱ ባልቴት ሆነ፣ ሁሉን ትቶ ለእግዚአብሔር ለማገልግል ወሰነ፣ በትላተሎልኮ ቤተ ክርስትያን በየዕለቱ እያስቀደሰ በትምህርተ ክርስቶስም እየተሳተፈ መኖር ጀመር። ከዕለታት ኣንድ ቀን ቅዳሜ ታሕሣሥ 9 ቀን 1531 ዓም ጥዋት ለቅዳሴ ሲሄድ ተፐያክ በሚባል ተራራ ሲደርስ ብዙ ወፎች ኣብረው እያዘሙ ሰምቶ ደስ ብሎት ሲያዳምድ ዜማው ወዲያው በድንገት እንደመጣው በድንገት ቆመ፣ ኣንድ መልከ መልካም ልጃገረድ በቋንቋው ኽዋን ድየጎ ስትል ጠራችው፣ የተከበርክ ልጄ እወደሃለሁ፣ ማን መሆኔን እንድታውቅ እፈልጋለሁ፣ እኔ ሕይወቱን የሰጠ የኣንዱ እውነተኛ ኣምላክ እናት ድንግል ማርያም ነኝ፣ እርሱ የሰማያትና የምድር ፈጣሪና ጌታ ነው፣ እርሱን በፍቅሬ በርኅራኄየ በእርዳታየና በጥበቃየ ለመላው ሕዝብ ለመስጠት በሁላቸው እንዲታወቅ በዚሁ ቦታ እንድገልጠው እወዳለሁና በዚህ ቦታ ቤተ መቅደስ እንዲሰራልኝ እፈልጋለሁ። እኔ እውነተኛ የምሕረት እናት ነኝ፣ ያንተው እናት ነኝ፣ በዚህ ምድር ለሚኖሩ ሁላቸው እናት ነኝ፣ እኔን ለሚወዱና ለሚለምኑ እንዲሁምእኔን ለሚፈልጉና እምነታቸውን እኔ ጋር ለሚጥለው ለመላው የሰው ልጅ እናት ነኛ። በዚህ ቦታ ልቅሶኣቸውና ሓዘናቸው ልሰማ ነኝ፣ ሁላቸውን በልቤ እወስደዋቸዋለሁ፣ ሥቃዮቻቸው ቁስሎቻቸውና ሓዘናቸውን እፈውሳለሁ፣ ስለዚህ ተሎ ብለህ ወደ ተኖኽቲትላን ሂድና ለጳጳሱ ያየሀውንና የሰማሀውን ንገረው’ ኣለችው። ኽዋን ድየጎ ወዲያውኑ ቤተ ጳጳሱ በሚገኝበት በፍራቸስካውያን የኣባ ፍራይ ኽዋን ደ ዙማራጋ ገዳም ሄደ፣ ኣገልጋዮቹ ብዙ ካዋረዱት በኋላ ከኣቡኑ ጋር ለመገናቸት ዕድል ኣገኘ። ጳጳሱ በጥሩ ሁኔታ ቢቀበሉትም ተጠራጠሩ ስለዚህ ጉዳዩን እንደሚያጠኑት ኣመልክተው ሌላ ግዜ እንዲመለስ ጠየቁት። ኽዋን ተስፋ ቆርጦ ወደ ተራራ ተመለሰ፣ እመቤታን ድንግል ማርያምም ለሁለተኛ ግዜ እዛ ስትጠባበቀው ኣገኛት፣ እርሱን ግምት የሚሰጠው ስለሌለ መልእክትዋን ሊያደርስ የሚችል ሌላ ታዋቂ ሰው እንድትልክ ለመናት። እርስዋም ‘ልጄ ሆይ ብዙ ልልካቸው የምችል ብዙ ሰዎች ኣሉ፣ ኣኔ ግን ለዚህ ተልእኮ ኣንተን መርጫለሁ፣ ስለዚህ ነገ ወደ ጳጳሱ ተመለስ፣ የላኩህ ዘወትር ቅድስ የሆንኩ የእግዚአብሔር እናት ድንግል ማርያም መሆኔን ንገረው፣ በዚህ ቦታ ቤተ ክርስትያን እንዲታነጽ ታላቅ ፍላጎት እንዳለኝም ንገረው፣’ ኣለችው።

በታሕሣሥ 10 ቀን እሁድ ዕለት ኸኣን ድየጎ እንደግና ወደ ጳጳሱ ቤት ሄደ፣ ኣሁንም ከብዙ ችግር በኋላ ከጳጳሱ ጋር ተገናኘ፣ ጳጳሱ እንደገና በመመለሱ ተገረሙ፣ እመቤታችንን ምልክት እንድትሰጠው እንዲጠይቃት ነገሩት። ኽዋን ድየጎ ወደ ተራራው ተመልሶ ለእመቤታችን ነገራት፣ እመቤታችንም ለትእምርት በነገታው እንዲመለስ ነገረችው።

ሆኖም ግን ኽዋን ወደ ቤት ሲመልስ ኣጎቱ ኽዋን በርናዲኖ በጥኑ ታሞ ያገኛልና ወደ እመቤታችን ከመመለስ ኣጎቱን እያስታመመ ቆየ። ብሶስተኛው ቀን ማክሰኞ ታሕሣሥ 12 ቀን ለኣጎቱ ምሥጢረ ቀንዴል የሚሰጥ ካህን ለመፈለግ ወደ ሳንቲያጎ ደ ትላተሎልኮ ቤተ ክርስትያን እንዲሄድ ተነሣ፣ ወደ ቤተ ክርትያኑ ለመድረስ ግን የግድ በተፐያክ ተራራ ማለፍ ነበረበት፣ ስለዚህ ዘወትር ከሚሄደው ከተራራው በስተምዕራብ ያለውን መንገድ ትቶ እመቤታችን እንዳታገኘው የበስተምሥራቅ በኩል መንገዱን ለመውሰድ መረጠ፣ በስተምሥራቁ በኩል ተደብቆ ሲሄድ ሳለ እመቤታችን ‘ትንሹ ልጄ ጉዳዩ ምን ሆነ? ስትል ታየችው፣ ኽዋን ባደረገው ሓፍረት ተሰማው፣ እመቤቴ ምን ገና ሳይነጋ ነቃሽ ደህና ነሽ ወይ ይቅሬታ ኣድርግልኝ፣ ኣጎቴ ታሞ ሊሞት እያቃሰተ ነው ለምሥጢረ ተክሊል ካህን እንዳገኝለት ልኮኛል፣ ኣጎቴ ታሞ ነው እንጂ ትናንትና ጥዋት የገባሁሽ ቃሌን ኣልለወጥኩም፣ ኣላት፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም ደግሞ፣ ታናሹ ልጄ ኣትቸገር፣ ኣትፍራም፣ እዚህ የለሁም እንዴ? እናትህስ ኣይደለሁምን? በከለላየና በጥበቃየ ሥር የለህምን? የደስታህ ምንጭስ ኣይደለሁም እንዴ? በእጆቼ ታቅፈህ ካፓየን ለብሰህ የለህም ወይ? ኣይዞህ ኣጎትህ በዚህ ግዜ ኣይሞትም፣ ኣሁኑኑ ጤናው ተመለሰለት። ኣሁን ምንም ምክንያት የለህም፣ ስለዚህ የምልህን ልብ ብለህ ለማዳመጥ ትችላለህ፣ በተራራው ጫፍ ላይ ውጣና በቦታው ከሚያብብቡ ኣበባዎች ለቅመህ ኣምጣልኝ’ ኣለችው። ኽዋን በልቡ በትሕሣሥ ወር ኣበባዎች ለማግኘት ከነጭራሹ የማይቻል ነው ብሎ ኣሰበ፣ ሆንም ግን ታዛዥ በመሆኑና የጽጌረዳ ኣበባዎችን እንደሚያገኝ በመተማመን ወደ ተራራው ጫፍ ወጣ። እንደእምነቱም ኣበባዎችን ኣገኘና የነበረው ብርድ ኣበባዎችን እንዳይጎዳቸው በማለት በልብሱ ሰብስቦ ያዛቸው፣ ወዲያውኑ ወደ እመቤታችን ተመለሰ፣ እመቤታችን ኣበባዎችን በደንም ኣስቀምጣ የልብሱን ታቸኛውን ጫፍ ኣስራ በኣንገቱ ኣንጠጥሎት እንዲሄድ በማዘዝ ‘ተመልከት ታናሹ ልቤጄ ይህ ወደ ጳጳሱ የምልከው ትእምርት ነው፣ ኣሁን ትእምርት እንደገኘ ንገረው የምፈልገውን ቤተ ክርስትያን በቦታው እንዲሠራ ንገረው፣ ከጳጳሱ በስተቀር ሌላ ማንም ሰው እንዳያየው ተጠንቀቅ፣ ወደ ጳጳሱ እስከትደርስ ድረስ ኣበባዎቹ ይዞ ያለውን ልብስ ኣጥብቀህ ያዘው፣ ለጳጳሱ እንዴት ኣድርጌ ተደብቀህ ለታመመው ኣጎትህ ምሥጢረ ተክሊል የሚሰጥ ካህን ለመፈለግ ስትሄድ በመንገድ እንዳገትሁህና የኣጎትህን መዳን በማረጋገጥ ኣበባዎችን ለመልቀም ወደ ተራራው እንደላኩህ እንዲሁም ኣበባዎችን እንዴት ኣድርጌ እንዳስተካከልክዋቸው ንገረው። ኣስታውስ ታናሹ ልጄ ኣንተ ታማኝ የእኔ እንደራሴ ነህ፣ ኣሁን ጳጳሱ ያልከውን ሁሉ ሊያምንህ ነው ኣለችው።

ኽዋን ድየጎ እንደገና ለሶስተኛ ግዜ ወደ ጳጳሱ ሄደና የሆነውን ሁሉ ነገረው፣ እመቤታችን እንዳለችውም ወሬውን ከጨረሸ በኋላ ኣበባዎችን ኣቅፎበት የነበረውን የጨርቅ ሁለቱን ጫፎች በፈታቸው ግዜ ኣበባዎቹ በወለሉ ወደቁ፣ ጨርቁም በኣንገቱ ተንጠጥሎ ቀረ፣ ጳጳሱ ከመንበራቸው ተነሡ ለእመቤታችን ክብር በጨርቁ ፊት ተንበረከኩ፣ በክፍሉ ከጳጳሱ የነበሩም እንደዛው። በጨርቁ ልክ ኽዋን ድየጎ የገለጻት የእመቤታችን ድንግል ማርያም ምስል ኣዩ፣ ኽዋን ድየጎ መልእክቱን ለማድረስ ከጳጳሱ እያለ በሕመም ወደ ሞት ተቃርቦ የነበረው ኣጎቱ በቅጽበት ቤቱ በሚያስደስት ብርሃን ሲያሸበርቅ ኣየ፣ ብርሃናዊት የሆነች በፍቅር የሞላች ወጣት ሴት በፊቱ ቆማ ከሕመሙ እንደሚድን ነገረችው፣ ኽዋን ድየጎን ወደ ጳጳሱ እንደላከችው ከእርሱም የእርስዋ ስእል እንደላከች ነገረችው፣ እኔንና ስእሌን የጓዳሉፐ እመቤት ብላችሁ ጥሩን፣ ኣለችው።

የግልጸቱ ዜና ወዲያውኑ በሁሉም ቦታ ደረሰ። የቦታው ሰዎች መልእክቱን ወዲያውኑ ተቀበሉት፣ ወዲያውኑ ለመቀበል ምክንያት የሆኑት ደግሞ እመቤታችን እንደእሳቸው የህንድ ወገን በመሆነ ናህዋትል የሚባል የኣዝተክ ቋንቋ በመናገርዋና ከእርሳቸው ኣንዱ ለሆነ ለኽዋን በመታየትዋ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በቶናንትዚን ቦታ በሆነው በተፐያክ በመታየትዋ የእውነተኛው ኣማልክ በመሆንዋና የክርስትና እምነት የኣዝተክን እምነት መታካት እንዳለበት ጥርት ያለ መልእክት በመስጠትዋ፣ በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ ነዋሪዎቹ በባህላቸው በስእልና በምልክት ብዙ ነገር ስለሚረዱ ቲልማ በሚባለው ጨርቅ የተሰጣቸው የእመቤታችን ስእልና መልእክት እውነተኛው ኣምላክ ለሰው ልጆች ደኅንነት ሕይወቱን ላንዴና ለመጨርሻ ስለሰዋ ያደርጉት የነበሩ ኣምልኮ ጣዕትና ያቀርቡት የነበረው የሰው ልጆች መሥዋዕትን የሚተካ በማግኘታቸው በደስታ ተቀበሉት። በዚህ ምክንያቱም ከ1531 እስከ 1538 በሰባት ዓመታት ውስጥ 8ሚልዮን የመክሲኮ ተወላጆች ካቶሊክ ሆኑ።

የእመቤታችንን ስእል የያዘው ተአምራታዊው ጨርቅ እስካሁን በቤተ ክርስትያኑ ይገኛል። የሰው ልጆች እስከሆን ድረስ መጠራጠር ኣይቀርምና፣ ብ1789 ዓም ሁኔታው ያስደነቅው ኣንድ ካህን ለኣንድ ሥነጥበባዊ ኽዋን ለብሶት እንደነበረው ልብስ በመውሰድ 11 ስእል እንዲሠራ ጠየቁት ሆኖም ግን በ7ዓመቱ ሁሉም ከጥቅም ውጭ ሆነ። እንድሁም በ1979 የቦታው የቤተ ክርስትያን ባለሥልጣናት የሳይንስ ሊቃውንት ባቀረቡላቸው ጥያቄ ሥእሉን ሳይንስ እንዲመረመር ፍቃድ ሰጥተው ተኣምራታዊ መሆኑ ተረጋገጠ። ይህንን ለ479 ዓመት በቦታው ባለው ሙቀትና እርጥበት ምንም ሳያበላሸው የቆየውን የእመቤታችን ትእምርት ዛሬም በየዓመቱ በሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ በቦታው እየተማላለሰ እምነቱን በማደስና ንስሓ በመግባት ይገኛሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.