2010-12-17 14:05:43

የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. መልእክት ለዓለም አቀፍ የሰላም ቀን


“የሃይማኖት ነጻነት የሰላም መንገድ ነው” በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ 44ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ምክንያት መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር የዜና እና የኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን የሰላም ቀን የሚታሰብበት ዕለት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ RealAudioMP3 ሁሌ በየዓመቱ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት እንደሚያስተላልፍ የሚታወቅ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው ዘንድሮ ለሚከበረው 44ኛው ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን የሃይማኖት ነጻነት የሰላም መንገድ ነው በሚል ርእስ ሥር የሚያስተላሉፉት መልእክት ትላትና በቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል የሰላም እና የፍትህ ጳጳሳዊ ምክር ቤተ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲላን ቱርክሶን በተገኙበት መድረክ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጦበት ይፋ ሆነዋል።

ቅዱስነታቸው የሰላሙን መልእክት በዓለማች ሃይማኖት መሠረት ያደረገው እየተስፋፋ ያለው ዓመጽ እና አድልዎ ላይ በማተኮር በኢራቅ ጸረ ክርስትያን ዓመጽ በተደጋጋሚ እየተከሰተ የክልሉ ማኅበረ ክርስትያን ለስደት እያዳረገ መሆኑ ዘክረው፣ በዓለማችን የክርስቶስ ተከታዮች ላይ የሚደርሰው ስደት እና መከራ አሳሳቢ መሆኑ ሲገለጡ፣ በሃይማኖት ምክንያት ለስደት እና ለመከራ ከተጋለጡት የሃይማኖት ምእመናን ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲታይ እጅግ የተጠቃው ክርስትያን ማኅበርሰብ መሆኑ በማስመር፣ በምዕራቡ ዓለም ሳይቀር ድምጸ አልቦ እና በተራቀቀ አሉታዊ ቅድም ፍርድ የተሸኘ አማኞችን በመቃወም ሥልት አልፎ አልፎ ታሪክ እና የብዙሃን ባህላዊ እና የማንነት መግለጫ የሆነው ጥንታዊ ክርስትያናዊ መለያ ትእምርቶችንም ጭምር በመካድ በአማኞች ላይ የጥላቻ መንፈስ አሉታዊ ቅድመ ፍርድ በማረማመድ ከሃይማኖት ነጻ የሆነ መንግሥት በሚል የሐሰት ከለላ ምክንያት በማህብራዊ ነክ ጉዳዮች ሥር ከሚፈጸሙት ኅብረ-ውይይቶች በማግለል ለዘርፈ ብዙ ችግር ተጋልጦ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክቱ የሃይማኖች ፅንፈኛነት እና ልቅ ዓለማዊነት የመጠናወት ቅንጅት እና ለሕጋዊ ኅብረአዊነት እና ለዓለማዊነት መሠረታዊ መመሪያ የሚቀናቀን እና እምቢ የሚል መሆኑ በማብራራት፣ ይህ ደግሞ የሰው ልጅ ሰብአዊነትን ዝቅ የሚያደርግ እና በሙላት የማይገልጠውን ራእይ ፍጽሙ አድርጎ በማቅረብ በሰው ልጅ ላይ የሚያስከትለው ችግር በጣም አደገኛ መሆኑ ገልጠዋል።

የሕግ ሥርዓት በሁሉም ደረጃ እርሱም በብሔራዊ አቀፍም ይሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሃይማኖታዊ ፅንፈኝነት ወይንም ጸረ ሃይማኖት የሆነውን ፅንፈኝነት ሲፈቀድ ወይንም ዝም ብሎ ማየት፣ የሕግ ሥርዓት ያለው ትክክለኛውን ትርጉም እርሱም የሰውን ልጅ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ ብሎም ማረጋገጥ የሚለውን ውሳኔ በመጣስ ኅብረተሰብ በማኅበራዊ ሥልጣን ላይ ብቻ በማተኮር የሃይማኖት እና የህሊና ነጻነት የሚገታ ብሎም ለሚደልዝ የፖለቲካው አምባገነናዊ ርእዮተ ዓለም ማጋለጥ ማለት መሆኑ ገልጠዋል። ስለዚህ ምእመናን አንዱ የመሆናቸው ክፍል የሆነው እርሱም በእምነታቸው መሠረት የሚገልጡት እና ይኽንን መሠረት በማኅበራዊ ሕይወታቸው ማጉላት የሚገባቸው ባህርይ እንዲያገሉ ለማስገደ በላያቸው ላይ የሚፈጸመው መደል ለመገመቱም የሚያዳግት ሆኖ እያለ ንገር ግን ሲከሰት ማየቱ እጅግ ያሳዝናል ካሉ በኋላ፣ ሰላም የተካነው ማኅበራዊ ሕይወት እንዲረጋገጥ የማያግዘው መከፋፈል እና የሰው ልጅ ክብር የሚሰርዝ ማመን እና አለ ማመን ያው ነው የእሴቶች ኅላዌ እና ቅድመ ተከታል ሂደታቸውንም ጭምር የሚክድ ተዛማጅ ግብረ ገብ፣ በዓለማችን እየተስፋፋ ነው። ሆኖም ግን መሠረታውያን የመመሪያ ጸጋዎ በእውነተኛ ሃይማኖት የሚገለጡት እሴቶች ከምሆናቸው አንጻር የሕዝብ ሃብት ናቸው። ስለዚህ ከሃይማኖት ነጻ የሆነው አወንታዊ ዓለማዊነት የሚያንጸባርቅ መንግሥት መቼም ቢሆን የሃይማኖች ማኅበራዊ ገጽታውን እውቅና መስጠት ይኖርበታል። ይህ ደግሞ በመንግሥት እና በሃይማኖት መካከል ውይይት እና ግኑንኘት ለማረጋገጥ መሠረት ነው ብለዋል። ስለዚህ የሚያምነው በማያምነው በተዘዋዋሪም የማያምነው በሚያምነው ላይ ተጽእኖ ሳይሆን መከባበር የተካነው የተሟላ ማኅበራዊ ውህደተ እንዲኖር የሚያግዝ መሆኑ በስፋት አስረድተዋል።

የሃይማኖት ነጻነት፣ በሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር ላይ የጸና ከነገር ባሻገር የሆነ ባህርይ ያለው መቼም ቢሆን ቸል ማለት እና ግምት አለመስጠት አይገባም። ስለዚህ ከሰው ልጅ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ዝርዝር የሃይማኖት ነጻነት ልዩ ሥፍራ ያለው ነው። የሃይማኖት ነጻነት ሲጠበቅ እና ሲከበር የሰውብአዊ መብት እና ፈቃድ ከነመሠረቱ በሙላት ይከበራል ማለት ነው። ነገር ግን የሃይማኖት ነጻነት ሲጣስ ፍትህ እና ሰላም ለሥጋት ይጋለጣሉ ብለዋል። ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ሃይማኖቱን በግልም በማህበርም የመኖር እና እምነቱን የመግለጥ መብቱ እና ፈቃዱ የተጠበቀ መሆን አለበት። እንዱ ሃይማኖቱን እንዲክድ ወይን ሃይማኖቱን ትቶ ሌላ ሃይማኖት ባስገዳጅ እንዲከተል እንዲቀበል ማድረግ ጸረ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ነው ብለዋል። የሃይማኖት ነጻነት የአማኞች ብቸኛ ጸጋ/ሃብት ሳይሆን የመላ ሰው ዘር ቤተሰብ ሃብት ነው፣ ስለዚህ ሕጋዊነት ያለው የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መመዘኛ ነው ብለዋል።

የሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ፣ የውሁዳን ሃይማኖት እና ማኅበርሰብ መብት እና ፈቃድ ዋስትና ነው። ብዙሃን የውሁዳን በሁሉም በግለጫው እና ባህላዊ መለያው አማካኝነት አምባገነን እንዳይሆን ይመራል፣ ያሳስባልም፣ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ክርስቶስ ብቸኛ እውነት ሕይወት እና መንገድ መሆኑ ካለት እምነት አኳያ በተለያየ መልኩ ከማንም የሚፈልቅ እውነት ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጣ መሆኑ በማመን የተዛማጅ ባህል ሳትከተል ሁሉም እምነቶች እንድ ናቸው ከሚለው ፈተና በመቆጠብ በተለያዩ ሃይማኖትች መካከል መግባባት እንዲኖር የውይይት ባህል ታነቃቃለች ብለዋል።

በዚህ አጋጣሚ ቅዱስ አባታችን እ.ኤ.አ. በ 1986 በሥመ ጥር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አነሳሽነት በአሲዚ ከተማ የተጀመረው ዓለም አቅፍ የሰላም ጸሎት ቀን ይኸው በሚመጣው ዓመት 25ኛ ዓመቱን እንደሚዘከር በማስታወስ፣ በዚህ የሁሉም ሃይማኖትች የጋራው የሰላም ጸሎት ተግባር፣ ሀይማኖች የአንድነት እና የሰላም አካፋይ እንጂ የልዩነት እና የግጭት ምክንያት አንዳልሆነ መመስከራቸው ቅዱስ አባታችን ገልጠዋል።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን የሁሉም ዓለም መንግሥታት በክርስትያን ላይ የሚፈጸመው ዓመጽ እንዲገታ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው በማስታወ፣ በእስያ በአፍሪቃ በመካከለኛው ምሥራቅ በተለይ ደግሞ በቅድስት መሬት የሚታየው ስደት እና መከራ አለ መቀባበል እና የጥላቻ መንፈስ እንዲወገድ በማቅረብ፣ ማኅበረ ክርስትያን የይቅርታ መንፈስ እና ምህረት ተግባር እንዲተጉ በማሳሰብ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተራራው ስብከት ተብሎ በሚገለጠው ብጽአን የሚያሰኙት ተግባር መኖር ይጠበቅበታል ብለዋል። የሚደርስብን ስቃይ እና መከራ በእምነት እና በተስፋ እንዲሁም የእግዚአብሔር ፍቅር በመመስከር መነገር አለበት። በምዕራቡ ዓለም በክርስትያን ላይ የሚነዛው የጥላቻ መንፈስ እና የሚገለጠው ተቃውሞ ክርስትያኖች ለእምነታቸው ታማኞች በመሆን በወንጌል ተመርተው የሚኖሩት ኑሮ የሚቀናቀን እና የሚያገል የሚያንቋሽሽ ተግባር መገታት አለበት፣ ስለዚህ የክርስትያኖች በማኅበራዊ ሕይወት ያላቸው አስተዋጽኦ መከበር ይኖርበታል ብለዋል።

ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፣ ስለዚህ ሰላም ግጭት እና ጦርነት ያለ መኖር ሁነት ማለት ሳይሆን ብሎም የጦር መሣርያ ወይንም የኤኮኖሚ የበላይነት የሚያረጋገጠው ሁነት ሳይሆን ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን በማወጅ ለሰላም የሰላም መሣሪያ እንዲሰጥ እንጂ ለመግደል እና ለማጥፋት ተብሎ በሚመረተው ጦር መሣሪያ አማካኝነት ሕይወት በማጥፋት ሰላም የሰላም መሣርያ ባልሆነ መሣሪያ ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ውድቅ መሆኑ በማመን፣ የግብረ ገብ መሣሪያ ማንገብ ለሰላም የሚደረገው ጥረት መሠረት ነው ያሉትን ሀሳብ በማስታወስ፣ የሃይማኖት ነጻነት ዓለምን የበለጠ የሚያደርግ የሚለውጥ የሚያድስ እውነተኛ የሰላም መሣሪያ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.