2010-12-17 14:08:22

ዓለም አቀፍ የሉተራን አቢያተ ክርስትያን ፈደራላዊ ኅብረት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና ጧት ዓለም አቀፍ ፈደራላዊ ሉተራን አቢያተ ርክስትያን ሊቀ መንበር መጋቤ ሙኒብ ዩናንን በሓዋርያዊ መንበራቸው ተቀብለው እንዳነጋገሩ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ቅዱስነታቸው ባሰሙት ንግግር ለአቢያተ ክርስትያን ውኅደት ታልሞ በኵላዊት ቤተ ክርስትያን RealAudioMP3 እና በሉተራን አቢያተ ክርስያን መካከል የሚደረገው ጥረት አመርቂ እየሆነ መምጣቱንም ገልጠው፣ ይህ ጥረት በጋራ ወንጌልን ለማበሰር አቢይ ደጋፍ ብቻ ሳይሆን ለሚሰጠው ምስክርነት እማኔ መሠረት ነው ብለዋል። በዚህ አጋጣሚም በሁለተ አቢያተ ክርስትያን የዛሬ አስራ አንድ ዓመት የጽድቅ አንቀጸ ሃይማኖት መሠረት የተደረሰው የጋራው ውሳኔ በክርስትያኖች መካለል ለተሟላ ውህደት መረጋገጥ ልዩ ምዕራፍ መሆኑ አብራርተዋል።

ለውህደት የሚደረገው ጉዞ ዘገምተኛ ቢሆንም ቅሉ ጥረቱ ታጋሽ የልዩነተ አጥር እያገለለ በተለያዩ አቢያተ ክርስትያን መካከል ያለው የጋራው ግኑኝነት እና ቲዮሎጊያዊ ውይይት ተጨባጭ እየሆነ መምጣቱንም የዛሬ አስራ አንድ ዓመት የጽድቅ አንቀጸ ሃይማኖት መሠረት የተደረሰው የጋራው ውሳኔ አቢይ ምስክር ነው ብለዋል። በእግዚአብሔር ድጋፍ እና ጥበቃ የሚከናወን የጋራ ጥረት ነው መሆኑ ገልጠዋል።

በመጨረሻም ለውህደት የሚደረገው ጥረት ለካቶሊኮች እና ለሉተራን አቢያተ ክርስትያን ምእመናን በጋራ የሕይት ወንጌል የክርስቶስ ብርሃን በሁሉም ማኅበራዊ ደረጃዎች እንዲጎላ እና እንዲያበስሩ አቢይ እድል እያሰጠ መሆኑ አስታውሰው፣ በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን መካከል የዛሬ አምስት ዘመናት በፊት የተፈጠረው ልዩነት ወደ አንድነት በማቅናት እየተደረገ ባለው ጥረት የዛሬ አስራ አንድ ዓመት በፊት የጽድቅ አንቀጸ ሃይማኖት መሠረት በተደረሰው የጋራው ውሳኔ ሳይገታ ለተሟላ ውህደት አልሞ ምሥጢረ ጥምቀት እና ቤተ ክርስትያናዊ ውህደት በሚሉት ርእሰ ጉዳዮች ጥረት እያደረገ ነው ካሉ በኋላ፣ ለሁሉም አቢያተ ክርስትያን ምእመናን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት የሰላም እና የደስታ ምክንያት እንዲሆን በመመኘት የክርስትያኖች አንድነት እንዲረጋገጥ የልዩነት አጥር ያገለለው የህደት መሠረት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የውህደቱን ጸጋ እንዲያድለን መጸለያቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.