2010-12-17 14:06:48

ብፁዕ አቡነ ዋርዱኒ፣ የቅዱስ አባታችን የሰላም መልእክት


ቅዱስ አባታችን ያስተላለፉት ጥር አንድ ቀን 2011 ዓ.ም. በይፋ የሚተላለፈውን 44ኛው የሰላም መልእክት በማስደገፍ በኢራቅ የባግዳድ ተባባሪ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕእ አቡነ ሽለሞን ዋርዱኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ RealAudioMP3 በመልእክቱ ቅዱስነታቸው የሰላም ጥሪ ሲያቀርቡ በቅድሚያ በኢራቅ ያለው ወቅታዊው ሁኔታ እና ለስደት እና ለተለያየ ዘርፈ ብዙ ችግር ተጋልጦ ላለው የአገሪቱ ክርስትያን ማህበርሰብ በማሰብ ያሰፈሩት ቃል፣ በእውነት የሚያዳምጥ ልብ እና የሚሰማ ጆሮ እንደሚያስፈልገው በመግለጥ፣ የኢራቅ ማኅበረ ክርስትያን ልዩ መብት እና ፈቃድ ሳይሆን እንደማንኛው ሰው ሰብአዊ መብቱ እና ፈቃድ ነው የሚጠይቀው፣ ስለዚህ በአገሩ መብቱ እና ፈቃዱ ተጠብቆለት እንዲኖር ነው ለአገሩ መንግሥት አብየት የሚለው፣ የኢራቅ መንግሥት የክርስትያኖች መብት እና ፈቃድ እንዲከበር የገባው ቃል እግብር ላይ ውሎ ለማየት እንፈልጋለን ካሉ በኋላ፣ ኤውሮጳ በተለያዩ አገሮች የሚታየው ጸረ ሰብአዊ መብተ እና ፈቃድ ተግባር እንዲወገድ አቢይ ሚና መጫወት እንደምትችል ገልጠው፣ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ በሚጣስባቸው አገሮች ያለው ማኅበራዊ ሁኔታ ሁሉም የሚያውቀው ነው ስለዚህ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መስፋፋት ለሰላም መሠረት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.