2010-12-16 17:07:16

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስኣስተምህሮ(15.12.10)


ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆላስያስ ሰዎች ከጻፈው መልእክት 1፣24 ‘አሁን በመከራዬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፥ ስለ አካሉም ማለት ስለ ቤተ ክርስቲያን በሥጋዬ በክርስቶስ መከራ የጐደለውን እፈጽማለሁ። ስለ እናንተ እንደ ተሰጠኝ እንደ እግዚአብሔር መጋቢነት፥ የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽሜ እንድሰብክ እኔ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ሆንሁ። ይህም ቃል ከዘላለምና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ የነበረ ምሥጢር ነው፥ አሁን ግን ለቅዱሳኑ ተገልጦአል።’

ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፣ የዛሬ ትምህርተ ክርስቶስ ስለ ቅድስት ቨሮኒካ ጁልያኒ ይናገራል። ቅድስት ቨሮኒካ በዚሁ ወር ከ350 ዓመታት በፊት የተወለደች የካፑቺን ድኻ ክያራ ኣባልና ባህታዊ ነበሩ። በጥምቀት የተቀበለችው ቨሮኒካ የሚል ስም ከቤተ ክርስትያን ቅዱስ ባህል ከምትገለጠው የኢየሱስን ፊት በመሓረም በማጽዳት የጌታን ስእል በመህረብዋ እንዳገኘች ይህችም ቅድስት የተሰቀለ ጌታን ምስል ታቀርብናለች፣ ቅድስትዋ በተለያዩ ግዝያት በሰቂለ ኅሊና ከጌታ ጋር በነበራት ፍቅርና ግኑኝነት የእርሱን የእሾህ ኣክሊል በራስዋ በመድፋት ቅድስ ቊስሎቹን ተቀበለች። በየዕለቱ የሚያጋጥማዋትን ነገሮች ትመዘገብበት ከነበረችበት የየቀን መዝገብዋ እንደሚያመለክተው፣ የቅድስት ቨሮኒካ መንፈሳውነት ክርስቶስን ማእከል ያደረግና እንደ ንጽሕት ሙሽራ በክርስቶስ ፍቅር የተሳሳረ ነበር፣ በመሆኑም ሁሉን ነገር በክርስቶስ ፍቅር ዓይን ትመለከተው ነበር። ይህ ኣመለካከት በሕማማቱ በመገለጡ እርስዋም እንደ እርሱ ኢየሱስ ለነፍሳት ድኅነት ኣባቱ ጋር ባቀረበው መሥዋዕት ለመሳተፍ በቃች። ለመጽሓፍ ቅዱስ የነበራት ፍቅር ለቤተ ክርስትያንን በነበራት ፍቅርና በሱታፌ ቅዱሳን በነበራት ኃይለኛ ስሜት ላይ የተመሠረተ ነበር። የቨሮኒካ ጠንካራ ሰቂለ ኅሊናዊ ሕይወት በቃላትዋ ሊገለጥ ይችላል፣ በሞት ኣፋፍ ላይ ሳለች ‘ፍቅርን ኣገኘሁ’ ብላ ነበር።

የቅድስት ቨሮኒካ ሕይወትና ትምህርት ከጌታና ከቤተ ክርስትያን ያለንን ኣንድነትና ፍቅር በማሳደግ ከክርስቶስ ጋር ስለ ኃጢኣተኞች ደኅንነት እንድናስብ ይርዳን።’








All the contents on this site are copyrighted ©.