2010-12-16 17:08:29

የር.ሊ.ጳ ሐዋርያዊ ጉብኝት በጀርመን


እ.አ.አ በ2011 ዓም ከመስከረም 22 ቀን እስከ መስከረም 25 ቀን ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በጀርመን ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የጀርመን ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ ኣስታወቀ።

እስካሁን በተመለከተው የቅዱስነታቸው የ2011 ዓም መርሃ ግብር መሠረት ቅዱስነታቸው ኣራት ዓለም ኣቀፍ ሐዋርያዊ ጉዞዎችና ሌላ ኣራት በኢጣልያ ኣገር ሰበካዎች በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ያካትታል።

እፊታችን ግንቦት 7 እና 8 ቀን በኣኲለያና ቨነዝያ ሐዋርያዊ ግብኝት ያደርጋሉ፣ ይህ ጉብኝት ከስመ ጥር የሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ካደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ከ26 ዓመት ብኋላ እንደሚከናወን የቨነዝያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኣቡነ ኣንጀሎ እስኮላ ገልጠው ነበር።

ሰኔ 4 እና 5 ቀን ክሮኣስያን ይጎበኝሉ፣ በዚሁ ሐዋርያዊ ጉብኝት ቅዱስነታቸው በብፁዕ እስተፒናች መቃብር እንደሚጸልዩም ተልክተዋል። ከሁለት ሳምንታት በኋላ ሰኔ 19 ቀን የሳን ማሪኖ ሞንተፈልትሮ ሰበካን ይጐበኛሉ። ይህንን ጉብኝት ኣስመልክተው የሰበካው ጳጳሳ ብፁዕ ኣቡነ ልዊጂ ነግሪ ‘ቅድስነታቸው እዚህ የሚመጡት የክርስትያን ቅዱስ ባህል እንደገና ለማሳደስ በጥሩ ጉዞ ያለች ቤተ ክርስትያንና በብርቱ ትግል ያለ ማኅበረሰብን በማግኘት ለማበረታት የሚደረግ ጉብኝት ነው’ ብለው ገልጠውታል።

ሌላው ዓለም ኣቀፍ ሐዋርያዊ ጉዞ ደግሞ፣ ብዙ የዓለም ወጣቶች በጉጉት የሚጠባበቁት ነሐሴ ወር የሚደረገው ዓለም ኣቀፍ የወጣቶች ቀን ለማክበር በእስፓቻ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ነው። የ2011 ዓለም ኣቀፍ የወጣቶች ቀን ‘በኢየሱስ ክርስቶስ የተመሠረቱና የታነጹ፣ በእምነት የጸኑ’ በሚል መሪ ሐሳብ ከነሐሴ 18 እስከ ነሐሴ 21 ቀን በማድሪድ ይካሄዳል።

እፊታችን መስከረም የሚደረጉ ሁለት ሐዋርያዊ ጉዞዎች ኣሉ፣ መስከረም 11 ቀን የኣንኮና ሰበካን ይጎበኛሉ፣ የጉብኝቱ ምክንያቱም በቦታው የሚደረገው ሃገራዊ የቅዱስ ቊርባን ኮንግረስ ለማጠቃለል ነው። ከመስከረም 22 እስከ 25 ቀን ደግሞ ይህ ትናንትና በጀርመን ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ የተገለጠ በጀርመን የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ይደረጋል።

የ2011 ዓም በኢጣልያ የሚያደርጉት የመጨረሻ ጉዞ ጥቅምት 9 ቀን በላመዝያ ተርመና በሰራ ቸርቶዛ ሳን ብሩኖ በኢጣልያ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ግብኝት ሲሆን በዓለም ኣቀፍ ደረጃ ደግሞ ከኅዳር 18 እስከ 20 ቀን በበኒን የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ይሆናል። የዚህ ጉዞ ምክንያት የኣገሪቱ የስብከተ ወንጌል የ150ኛ ኢዮቤል መሆኑን ከቅድስት መንበር የመጣ ዜና ኣመልክተውል። በዚህም የቅዱስነታቸው የ2011 ዓም ሐዋርያዊ ጉዞዎች መርሃ ግብር ኣራት ዓለም ኣቀፍ ሐዋርያዊ ጉዞዎችና ሌላ ኣራት በኢጣልያ ኣገር ሰበካዎች በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝቶች እንደሚፈጸም ተመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.