2010-12-16 17:09:34

በሕመም የሚገኘውን ሰው ሰብአዊ ክብሩን በመጠበቅ መፈቀር ኣለበት።


በሕመም የሚገኘውን ሰው ሰብአዊ ክብሩን በመጠበቅ መፈቀር ኣለበት። ይህንን ያሉት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዝዮ በርቶነ ትናንትና በቪላ ጁሰፒና ሮም ከተማ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ከተመሠረተ መቶኛ ዓመቱ ለማስታወስ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ነበር።

ብፁዕነታቸው የዚህ መሥራቅ ቅድስት ሮዛ በማስታወስ በተለይ እርስዋ ለሕመምተኞች የነበራትን ፍቅር በማትኰር ቃላትዋን ደግመዋል፣ ቅድስት ሮዛ የምታቀርበው ጥሪ፣ ሕመምተኛን ሰብአዊ ክብሩን በመጠበቅ ማፍቀር ተቀዳሚ ግዳጃችን ነው ሲሉ ጥሪውን ደግመዋል።

የሆስፒታል መሥራችዋ ቅድስት ሕመምተኛን በክርስቶስ ዓይን ትመለከተው እንደነበርና ሕመምተኛን ከመታመሙ በፊት እንደነበረው መታየት ኣለበት ምክንያቱም ታሞ የሰው እርዳታ ከመፈለጉ በፊት የማይደመሰስ ሰብአዊ ክብር የነበረው ክቡር ፍጥረት መኖሩን መዘንጋት የለብንም። ዛሬ ባለንበት ዘመን ግን ሰውን የምንመዝነው በሰብአዊ ክብር ሳይሆን በገነዘቡና ባለው ሃብት ስለሆነ ሰብአውነትን ኣደጋ ላይ በመጣል እንገኛለን። እውነቱን ለመናገር እንዲህ ያለ ኣስተሳሰብ ይዞ እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ ሰውን ማገልገል ኣንችልም። እንዲህ ስለሆነም ነው የዘመናችን ሰው ሃብትም ይኑረው በውሳጣዊ ብቸኝነት እየተሰቃየ ያለው። ስለዚህ በታመመው ኣካል የእርዳታ መስጠት ጥሪ እንደሚቀርብልን ይህም እያንዳንችን ማስታወስ ያለብን በሕመም ስትሰቃይ የምትገኝ ነፍስ የምታቀርበው ጥያቄ መሆኑን ኣለመዘንጋት ያስፈልጋል። ሲሉ በሕመም ለሚሰቃዩ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን በፍቅር መቅረብ እንዳለብን ኣደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.