2010-12-15 14:15:48

የቫቲካን ሁለተኛ ጉባኤ Lumen Gentium-ብርሃነ አሕዛብ


በቫቲካን ረዲዮ ኢየሱሳዊ ካህን ኣባ ዳሪዩስ ኮዋልችይክ ስለ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በማስመልከት የጀመሩት አዲስ የስርጭት መርሃ ግብር በመቀጠል ትላትና Lumen Gentium-ብርሃነ አሕዛብ በሚል ርእስ ሥር ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ስለ ቤተ ክርስትያን ጉዳይ በተመለከተ የደነገገው የአንቀጸ ሃይማኖት ውሳኔ በማስደገፍ በሰጡት ጥልቅ ማብራሪያ፦ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ RealAudioMP3 አበው ቤተ ክርስትያን ስለ ገዛ እራሽ ምን ትያለሽ የሚል ጥያቄ በማቅረብ፣ ቤተ ክርስትያን በዚያኑ ቅዱስ ጉባኤ ሥር ስለ ገዛ እራስዋ በመናገር እራስዋን የእዚአብሐር ሕዝብ፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አካል የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ/ማደሪያ እባላለሁ ብላ በማስተዋወቅ መልስ እንደሰጠች ገልጠው፣ ስለዚህ “እኛ” ቤተ ክርስትያን ነን፣ ይህ ደግሞ መሪያችን በሮማ መቀመጫው በሆነው ሥር የምንመራ የአንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት አባላት በመሆን የምንታቀፍ ማለት ሳይሆን፣ ቅድስት ሥላሴ በሦስት አበይት ተጨባጭ መሠረት ርነርሱም ቃል፣ ቅዱሳት ምሥጢራት እና የፍቅር-ሥራ (ግብረ-ሠናይ) በሚሉት ላይ የጸና አንድ ማኅበረሰብ ሊኖረው ፈቀደ (ፈለገ) ከሚለው ፍቃድ የመነጨ ነው። ስለዚህ ማንኛውም አማኝም ይሆን ኢአማንያን ስለ ቤተ ክርስትያን ሊናገር የሚፈልግ ከዚህ ቤተ ክርስትያን ስለ ገዛ እራሷ ካላት ቤተክርስትያናዊ ርእሰ ግንዛቤ በምን ተአመር ግምት ከመስጠት ውጭ መናገርም ሆነ ማሰብም አይችል። ይኸንን ቤተ ክርስትያን ስለ ገዛ እራሷ ያላት ርእሰ ግንዛቤ ግምት የማይሰጥ ቤተ ርክስትያናዊ አገላለጥ እና አነጋገር ጨርሶ ሊኖር እና ሊታሰብ የማይቻል ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቤተ ክርስትያን ተመሳሳይ ፍላጎት ያላፈቸው በጋራ በማምረት እና ምርቱን ለገበያ በማቅረብ የሚረኩ የሰዎች ስብስብ ማለት ሳይሆን በባህል እና በዜግነት የተለያዩ ቢሆኑም ቅሉ ከእግዚአብሔር ጋር ባላቸው ግንኝነት አማካኝነት የሚጸና ማኅብረሰብ ማለት ነው ሲሉ በማስረዳት፣ የሰጡት ማብራሪያ ይኸንን የቫቲካን ሁለተኛው ጉባኤ ስለ ቤተ ክርስትያን የሰጠው ትንተና የሚያጎላ ነው ካሉ በኋላ፣ ቤተ ክርስትያን ስንል ር.ሊ.ጳ ካህናትን ብቻ ማሰብ የለብንም ስለዚህ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሕዝበ እግዚአብሔር ነቢይ ካህን እና ንጉሣዊ ቤተ ሰብ ለመሆን ለቅድስና የተጠራ ነው የሚለውን መግለጫው ዳግም ለማስገንዘብ ችለዋል። ስለ ቤተ ክርስትያን ከመናገራችን በፊት ይህች ቤተ ክርስትያን የበለጠች ወይንም ደካማ/ሐጢአተኛ የሚያደርጋት እኛ የምንኖረው እና እግብር ላይ የምናውለው ቤተ ክርስትያናዊ መሆናችን ለመግለጥ የምንከተለው መንገድ ነው። ምክንያቱም እርሷ ዘወትር ቅድስት ነች ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.