Home Archivio
2010-12-15 14:18:33
ኢጣሊያ
የኢጣሊያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ በሳቸው የሚመራው የነጻነት ሕዝብ የፖለቲካ ሰልፍ አጋጥሞት ባለው ውስጣዊ መከፋፈል ምክንያት በተለይ ደግሞ ከበርሉስኮኒ ጋር የነጻነት ሕዝብ የፖለቲካ ሰልፍ መሥራች
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር ጃንፍራንኮ ፊኒ የበርሉስኮኒ የፖለቲካ ሂደት ግልጽነት እና ዴሞክራሲያዊ አሠራር የጎደለው ነው በማለት ከፖለቲካው ሰልፍ በመውጣት አንድ አዲስ የፖለቲካ ሰልፍ በማቆማቸው ምክንያት በበርሉስኮኒ የሚመራው መንግሥት የአብላጫ ሙሉ ብቃቱን እንዲያጣ በማድረጉ እና ይኽ ደግሞ በርሉስኮኒ ከስልጣናቸው እንዲወርዱ ያስከተለው ጥያቄ መሠረት በሕግ መወሰኛ የበላይ ምክር ቤተ እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት ትላትና የመንግሥታቸው የእማኝነት ጥያቄ በማቅረብ በሕግ መወሰኛዉን የበላይ ምክር በከፍተኛ ድምጽ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደግሞ በጥቂት የድምጽ ልዩነት አማካኝነት መንግሥታቸው ከመውደቅ ተላቆ ቀጣይነት እንዲኖረው እማኝነትን አግኝተዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.