2010-12-15 14:14:23

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፣ ለእናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘ ካልኩታ መታሰቢያ


እ.ኤ.አ. ነሐሴ 26 ቀን 1910 ዓ.ም ተወልደው እ.ኤ.አ. መስከረም 5 ቀን 1997 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት እ.ኤ.አ. ጥቅትም 19 ቀን 2003 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ብፅና የታወጀላቸው እናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘ ካልኩታ RealAudioMP3 የተወለዱበት 100ኛ ዓመት መታሰቢያ ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. እፊታችን ታሕሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ በእናቴ ብፅዕት ተረዛ ዘ ካልኩታ የፍቅር ደናቅል ማኅበር ለሚረዱትን ድኾች የምሳ ግብዣ በማቅረብ አብረው የምሳ ግብዣ ተቋዳሽ እንደሚሆኑ የቅድስት መንበር መግልጫ አመለከተ።

እ.ኤ.አ. ጥር 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ለባዕለ አስተርእዮ ዋዜማ ቅዱስነታቸው ሮማ የሚገኘው ጀመሊ ሆስፒታል ከቀትር በኋላ በመጎብኘት እዛው በሕጻናት ማከሚያ ቤት ለሚገኙት ህሙማን ሕፃናት ገጸ በረከት እንደሚሰጡ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.