2010-12-13 16:44:56

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የመልኣከ እግዚአብሔር ጉባኤ ኣስተምህሮ(12.12.2010)


ቅ.ኣ.ር. ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትናንት በሮማ ኣከባቢ በሚገኘው የቅዱስ ማክሲሚልያኖ ዘኮልበ ቍምስና ሓዋርያዊ ግብኝት ፈጽመው ከተመለሱ በኃላ እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ የዕለቱን ቃለ እግዚአብሔር በመመርኮስ ኣስተምህሮ በማቅረብ ከምእመናንና ከተለያዩ ቦታዎች ከመጡ ነጋድያን ጋር ጸሎተ መልኣከ እግዚአብሔር ኣሳርገዋል። በመጨረሻም ምእመናን በቤታቸው በሚያደርጉት የበዓለ ልደት ማስታወሻ ግርግም የሚያስቀምጡት የኢየሱስ ሕፃን ምስሎችን ባርከዋል፣

ቅዱስነታቸው ያቀረቡት ኣስተምህሮ የሚከተለው ነው፣ ‘ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፣ በዚሁ የዘመነ ምጽአት ሶስተኛ እሁድ፣ ሥርዓተ ኣምልኮኣችን ከቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ መልእክት 5፣7 ‘እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ’ በሚለው ጥቅብ እንድናስተነትን ይጠራናል። በዘመናችን ከሁሉም በላይ የጽናትና የመታገሥ ኣስፈላጊነትን መጥቀስ ኣስፈላጊ ይመስለኛል። እነኚህ ኃይላት ኣባቶቻችን በእምነት ጉዞኣቸው የተጠቀሙባቸው ፍቱን የቅድስና መሣርያዎች ናቸው፣ ባለንበት ግዜ ግን ዓለማችን ከመታገስና ከጽናት ይልቅ በትዕቢት ተውጦ ከኣዳዲስ ነገሮች ጋር ኣለኣቅዋም እየተለዋዉጡ መሄድን ይመርጣል። ይህንን እንደ የዘመናችን ሥልጣኔ የሚታየውን ነገር ሳንነካ የዘመነ ምጽአት ግዜ የሚያቀርብልንን ጥሪ ያዳመጥን እንደሆነ የውስጣንችን ኃይልን ማጠንከር እንዳለብን ለዚህ መጠባበቅ ኃይል ማለት ደግሞ የምንጠባበቀው ይዘገይ ይሆናል የሚል ተስፋ ሳንቈርጥ ልንጠብቀው እንዳለብን እንዲያው መተማመን በተሞላበት ተግባር ለጌታ መምጣት እንድንዘጋጅ ያስፈልጋል።

ቅ.ያዕቆብ ሐዋርያ የገበሬው ምሳሌ በማቅረብ ‘እነሆ፥ ገበሬው የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እስኪቀበል ድረስ እርሱን እየታገሠ የከበረውን የመሬት ፍሬ ይጠብቃል። /a>  እናንተ ደግሞ ታገሡ፥ ልባችሁንም አጽኑ፤ የጌታ መምጣት ቀርቦአልና።’ ይለናል። ይህ የገበሬ ትዕግሥትና መጠባበቅ ምሳሌ ሁሉን ይገልጣል፣ በእርሻ የሚተዳደር ዘር ከዘራ በኋላ በጽናትና በትዕግሥት ለወራት ያህል ይጠባበቃል፣ በዚሁ የመጠባበቅ ግዜ በዝናሙና በኣየር ንብረት ታግዞ፣ ዘሩ ግዜውን ጠብቆ የመብቀል የማደግና ወደ ፍሬ የመድረሱ ዑደትን ያካሄዳል፣ ገበሬ ከዕድል ጋር በከንቱ የሚታገል ኣይደለም፣ በተመዛዘነ መንገድ ኣእምሮንና እምነትን የሚያጣምር ጥሩ ኣብነት ነው፣ ባንድ በኩል የተፈጥሮን ሕግ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ መደረግ ያለበትን ጥንቃቄና እንክብካቤ በተገባ መንገድ ያከናውናል፣ በሌላው በኩል ደግሞ ኣንዳንድ መሠረታውያን ነገሮች በቁጥጥሩ ሥር ሳይሆን በኣምልክ እጅ ስለሆኑ በኣምላክ ኣሳቢነት ይተማመናል። ትዕግሥትና ጽናት የሰው ልጅ ኃልፊነቱን እንዲዋጣ የሚያደርገው ጥረትንና በእግዚአብሒር ኣሳቢነት መተማመንን ኣጣምረው የሚይዙ ናቸው።.

ቅዱስ መጽሓፍ ‘ልባችሁን ኣበረታቱ’ ይለናል፣ ይህንን እንዴት ልናደርገው እንችላለን? በፍጥረታቸው ደካማ ለሆኑና ከበውን ባሉ ነገሮች የሚርበተበቱ ልቦቻችን እንዴት ኣድርገን ልናጠነክራቸው እንችላለን? እርዳታ ሁል ግዜ ኣለን፣ እርዳታችን የእግዚአብሔር ቃል ነው፣ እንዲያው ሁሉ ነገር ሲያልፍና ሲያከትም የጊታ ቃል ግን ኣያልፍም። የኑሮ ጉዳዮች የመጥፋት ስሜት በመፍጠር ያለን እርግጠኝነት ሁሉ እንደሚፈርስ ቢያስመስሉትም መሪ የሚሆንና ኣቅጣጫችንን በማስያዝ ወደ ደሴት የሚያደርሰን መልኅቅ ኣለን። እግዚአብሔር በስሙ እንዲናገሩን የመረጣቸው ነቢያት ለዚህ ናቸው የሚያገልግሉ። የሰው ልጆች ደስታን በተሳሳተ መንገድ በየጎዳናው በሚገለጡ ነገሮች ሲፈልጉ ነቢይ የሆነ ሰው ግን እግዚአብሔርን በመተማመን ስለ ተመሠረተ የማያደናግር እውነተኛ ተስፋን በመስበክ ደስታውና ኃይሉን ከጌታ ቃል ያገኘዋል። እያንዳንዱ ክርስትያን በምሥጢረ ጥምቀት ኃይል የትንቢት መብት ተሰጥቶታል፣ ስለዚህ እያንዳንዳችን መለኮታዊው ቃለ እግዚአብሔርን በጽናት በማዳመጥ ይህንን የትንቢት መብት እንደገና ሊያገኘውና ሊመግበው ይችላል። ይህንን ለማድረግ ቃለ እግዚአብሔር እንደሚፈጸም በማመንዋ ብፅዕት የተባለችው ድንግል ማርያም ትርዳን።ካሉ በኋላ ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ኣሳርገዋል።

ቅዱስነታቸው ከጸሎቱ በኋላ ዘወትር በዚሁ የዘመነ ምጽኣት ግዜ እንደሚያደርጉት እያንዳንዱ ቤተ ሰብ በቤቱ በሚያደርገው የበዓለ ልደት ማስታወሻ ግርግም የሚያስቀምጡት የኢየሱስ ሕፃን ምስሎችን ባርከዋል፣ ሰላምታ ሲያቀርቡም የኢየሱስ ሕፃን ምስሉን በግርግም በምታኖሩበት ግዜ ስለ ር.ሊ.ጳ ስለ ሓሳቡ እንድትጸልዩ ኣደራ በማለት ተማጥነዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.