2010-12-08 13:28:55

አርጄንቲና ለፍልስጥኤም እውቅና ሰጠች


እ.ኤ.አ. የ1967 ዓ.ም. የፍልስጥኤም ድንበራዊ መልክዓ ምድር መሠረት ከብራዚል በመቀጠል አርጀንቲና ለአገረ ፍልስጥኤም እውቅና መስጠትዋ ሲገለጥ፣ ባለፈው ሳምንት ቦሊቪያ ኮስታር ሪካ ኩባ ኒካራጉዋይ እና ቨነዝዌላ ተመሳሳይ ውሳኔ RealAudioMP3 ማስተላለፋቸው ለማወቅ ሲቻል በሚቀጥለው ሳምንት ኡራጉዋይ ተመሳሳይ ውሳኔ ታስተላልፋለች ተብሎ ይጠበቃል። እስራኤል የነዚህ የላቲን አመሪካ አገሮች ለፍልስጥኤም አገረ እውቅና የሰጡበት ውሳኔ ጣልቃ ገብነት ነው በማለት እጅግ እንዳስቆጣት በይፋ አሰታውቃለች። ይን በ1967 ዓ.ም. የፍልስጥኤም ድንበር መግለጫ የሆነው መልክዓ ምድር መሠረት በማድረግ ነጻ የፍልስጥኤም አገር እውቅና የመስጠቱ ውሳኔ በማስመልከት በኢጣሊያ ሰላም ለመካከለኛው ምሥራቅ የተሰየመው ለዚያ ክልል ሰላም መረጋገጥ የሚያስችለውን መንገድ የሚያፈላልገው ማእከል ዋና አስተዳዳሪ ጃኒኪ ቺንጎሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም ለማረጋገጥ የሚደረገው የገላጋይነት ጥረት በእስራኤል አልቀበልም ባይነት ተግባር የሰላሙ ሂደት ዘገምተኛ ከመሆኑም አልፎ ባለበት የሚራመድ ሆኖ በሚታይበት በአሁኑ ወቅት፣ ፍልስጥኤም እ.ኤ.አ. በ1967 ዓ.ም. የፍልስእጥኤም ድምበራዊ ክልል መግለጫ መሠረት ነጻ የፍልስጥኤም አገር በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኝ ዘንድ የፍልስእጥኤም የራስ ገዝ መንግሥት ከዓረብ ሊግ ጋር በመተባበር ለተባበሩት መንግሥታት የበላይ ምክር ቤት ጥያቄ ለማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው ሲታወቅ፣ ሆኖም ግን ይህ የፍልስጥኤም ጥያቄ በተባበሩት መንግሥታት ቢቀርብ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ማንኛውም እስራኤል ጋር ሊያጋጭ ያስችላሉ የሚባሉትን ውሳኔዎች በተባበሩት መንግሥታት መድረክ እንዳይቀርብ በማሳሰብ ቢቀርብ ድምጽ በድምጽ የመሻር መብት መሠረት ውድቅ ያደርጋል የሚል ግምት ያለ በመሆኑ ብዙ አገሮች በግል አነሳሽነት የፍልስጥኤም ነጻ አገር በ 1967 ዓ.ም. የተመለከተው ድንበራዊ መልክዓ ምድር መሠረት እውቅና መሥጠት የሚለው በዓለም አቀፍ መድረክ ወሳኝ ከሆኑት አገሮች ጋር ለመሆን በብቃት ጎዳና ላይ የሚገኙት ብራዚል እና ቱርክ የሚያምኑበት ውሳኔ በመከተል ላይ ይገኛሉ።

ብራዚል በነዳጅ ማዕድን ሃብት እምቅ ኃይል የተላበሰች ስትሆን በብራዚል እና ቱርክ በተለምዶ የምዕራብ ኃይል ተብሎ የሚነገረው ፖለቲካዊ ሂደት ቀየር የሚያደርገው አዲስ አማራጭ የሆነ የፖለቲካ ሂደት ብቅ እያለ ነው። የ 1967 ዓ.ም. የፍልስእጤም ድንበራዊ ክልል መግለጫ ሰነድ የስድስቱ ቀናት ጦርነት ቀዳሜ መሆኑ እርሱም አረንጓዴ መሥመር ተብለው የሚጠሩትን ምዕራባዊ የዮርዳኖስ ዳርቻ ጋዛን እና የእየሩሳሌም ምሥራቃዊ ክልል ያጠቃለለ ነው። ይህ ታሪካዊ የፍልስጥኤም መልክዓ ምድር መግለጫ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ እና የደህንነት የበላይ ምክር ቤት የሚያምንበት ቢሆንም ቅሉ ባንጻሩ ግን ከዮርዳኖስ ጋር ለተደረሰው የሰላም ስምምነት መሠረት የሆነው አይነት የሰላም የስምምነት ሰነድ በእስራኤል እና በፍልስእጥኤም መካከል ቢረጋገጥ የሚበጅ ነው በሚል ውሳኔ ቢተካ ይሻልል የሚል ነው ሲሉ በማብራራት በሰጡት ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.