2010-12-08 13:26:27

ብፁዕ ካርዲናል ተታማንዚ፦ ስደተኛ ወንጀለኛ ማለት አይደለም


ትላትና በኢጣሊያ ሚላኖ ከተማ የከተማይቱ ጠባቂ ቅዱስ አምብሮሲዩስ በዓል በተከበርበት ዕለት የሚላኖ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲላን ዲዮኒጂ ተታማንዚ ለምእመናን እና ለከተማው ነዋሪ ሕዝብ ባስትላለፉት መልእክት፣ በቅርቡ በኢጣልያ RealAudioMP3 በተለያዩ ክልሎች በተፈጸሙት ወንጀል ምክንያት የጸጥታ ሃይሎች እያካሄዱት ባለው የወንጀለኛ የማጣራት ምርመራ አንዳንድ ስደተኞች ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ በማለት ያቀረቡት ገና መጣራት ያለበት የተጠርጣሪ ሀሳብ መሠረት ገና ጉዳዩ በወንጀል አጣሪ የበላይ ፍርድ ቤት በኩል ውሳኔ ሳይሰጥበት በደፈናው አንዳንድ ተመርማሪ ስደተኞች ወንጀለኛ አድርጎ መመልከቱ ስህተት ብቻ ሳይሆን ስደተኛ እና ወንጀልን አንድ አድርጎ የመመልከቱ ፈተና የሚያነቃቃ ነው። ስለዚህ ተጠርጣሪ ወይም ስደተኛ አንደ ወንጀለኛ እድርጎ አመመልከቱ ጅምላዊ ቅድመ ፍርድ ጸረ ሰብአዊ መብት እና ፍቃድ መሆኑ ማብራራታቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ብፁዕነታቸው በዓሉን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት፣ እንደ ቅዱስ አምብሮዚዩስ የእግዚአብሔር ቃል ዘሪዎች እና በቃሉ መሠረት ሕይወታችንን እንምራ ካሉ በኋላ፣ ሚላኖ ከተማ አለ ምንም ልዩነት እና አድልዎ አስተናጋጅ የኅብረ ባህል የኅብረ ሃይማኖት ማእከል ከተማ ነች ብለዋል።

በሌላው ረገድ የሚላኖ ከተማ የልማት ፖለቲካ የሕንጸት ቤተ ሰብ የኅብረተሰብ ማእከል መሆኑ በማሳሰብ የስደተኞች ጉዳይ የሚመለከቱት ርእሶች በመዳሰስ የከተማይቱ እድገት ድኾችን እና በጠና ድኽነት ሥር የሚገኙት ዜጎችን ማእከል የሚያደርግ ማንም የማያገል መሆን አለበት እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.