2010-12-08 16:43:25

በዓለ ፅንሰታ ለማርያም


ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ኣደባባይ ባስተማሩት የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ ኣስተምህሮ እንደገለጡት በፕያሳ እስፓኛ ኣደባባይ በሚገኘው ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ክብር ብታነጸው ኃውልት በዘልማድ በሚደረገው ሥርዓተ ጸሎተ ሰርክ ለመሳተፍና መሪ ቃል ለመስጠት ዛሬ ከቀትር በኋላ በሮም ሰዓት አቆጣጠር ለኣራት ሰዓት ሩብ ጉዳይ ከመንበራቸው ተነሥተዋል፣ እግረ መንገዳቸው በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስትያን በመቆም እዛው ተሰብስበው ለነበሩ ምእመናን ሰላምታ ኣቅርበዋል፣ ኣራት ሰዓት ተሩብ ፕያዛ እስፓኛ ደርሰዋል፣ ብዙ ካርዲናላትና ጳጳሳት ካህናት ደናግልና ምእመናን እንዲሁም የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት ‘ቱ ኤስ ፐትሩስ’ ኣንተ ጴጥሮስ በሚለው ጥንታዊው የላቲን ዜማ ተሸኝተው በታላቅ ክብርና ጭብጨባ ተቀበልዋቸውል።

ቅዱስነታቸው የክብር ቦታቸውን ከያዙ በኋላ መዘመራን ጥንታዊው የላቲን ዜማ ‘ቱ ኤስ ፐትሩስ’ አንተ ጴጥሮስ ነህ፣ በዚሁ አለት ቤተ ክርስትያኔን እገነባለሁ የሲኦል ኃይላትም በእርስዋ ላይ ድል ኣይነሱ፣ የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ ለአንተው እሰጣለሁ። ሲሉ የጸሎተ ሰርኩ መግቢያ መዝሙር ካዜሙ በኋላ ቅዱስነታቸው፣ በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ሲሉ ጸሎቱን በመክፈት የእመቤታችን እርዳታን ከተማጠኑ በኋላ ከሓዋርያው ጳውሎስ መልእክት ወደ ገላትያ ሰዎች 4፣ተነበበ። ሕዝቡ ንባቡን በጽሞና ካዳመጠ በኋላ ሊጣንያ ዘእግዚእትነ ማርያም በታላቅ መንፈሳውነት ኣሳርገዋል። ሁላቸው ኣብረው በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ ደግመው ቅዱስነታቸው እንደገና እንጸልያ በማለት ወደ እመቤታችን ተማጥነዋል።

ከዚህ በኋላ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ሰላምታና ትምህርት ኣቅርበዋል።

ውድ ወንድሞቼና ኣኅቶቼ፣ ዘንድሮም እንደቀጠሮኣችን በዚሁ በፕያዛ እስፓኛ ትልቁን የእመቤታችን በዓል ምክንያት በማድረግ ኣለ ኣዳም ኃጢኣት ለተፀነሰችውን ድንግል ማርያም ያለንን ክብር ለመግለጥ ተሰብስበናል። በዓሉን ለማክበር ከሩቅና ቅርብ እስከዚህ በመምጣት እዚህ ለምትገኙ እንዲሁም በረድዮ እና ተለቪዥን ለምትከታተሉ ሁላችሁ ልባዊ ሰላምታየን ኣቀርባለሁ፣ ዛሬ የሮማ ሕዝብ ለኢየሱስ እናት ያለውን ፍቅርና ኣክብሮት ምልክት በአበባ ጉንጉን ተከቦ ባለው በዚሁ ታሪካዊ ሓውልት እንገኛለን። ከአበባው የበለጠ እርስዋ የምትደሰትበት ሥጦታ የምናቀርበው ጸሎትና በልባችን ሆኖ የሚያስቸግረንን ሁሉ ለእርስዋ ማማጠናችን ነው። በዚሁ መንገድ የምናቀርባቸው ጸሎቶች የምስጋናና የልመና ናቸው፣ ምስጋና ስንል በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ለምናገኛቸው መልካም ነገሮች ከሁሉም በላይ ለእምነት ስጦታ እናመሰግናለን፣ ልመና ስንል ደግሞ ለተለያዩ ፍላጎቶች ለቤተሰብ ለጤና ለሥራ የምናቀርበው ስለት ነው። ሆኖም ግን በዚሁ ዕለት እዚህ በምንመጣበት ግዜ እኛ ከምናቀርበው ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የምንቀበለው እጅግ እንደሚልቅ ማወቅ ኣለብን። እርስዋ ለእያንዳንዳችን እንዲሁም ለሮማ ከተማና ለመላው ዓለም የሚሆን መልእክት ትሰጠናለች፣ የዚህች ከተማ ጳጳስ የሆንኩ እኔም በጽሞና ለማዳመጥ እዚህ እገኛለሁ፣ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁላችን ማርያም ምን ትለናለች? እርስዋ በማኅፀንዋ ተቀብላ ሥጋ ባለበሰችው በእግዚአብሔር ቃል ነው የምትናገረን፣ መልእክትዋ ሕይወትዋ ከሆነ ከኢየሱስ ሌላ ምንም ኣይደለም፣ ለኢየሱስ ምስጋና ይሁን፣ ኣለ ኣዳም ኃጢአት የተፀነሰችውም ለዚህ ነው፣ የእግዚአብሔር ልጅ እንደእኛ ሰው እንደሆነው ሁሉ እርስዋም ከኣባታችን ኣዳም ኃጢኣት እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን በነበረው የመዳን ዕቅድ ጠበቃት። በዚህ ደግሞ እመቤታችን ድንግል ማርያም እያንዳንዳችን ለመንፈስ ቅዱስ ሥራ ክፍት በመሆን ወደ የመጨረሻው ዓላማችን እንድንደርስ ጥሪ ታቀርብናለች፣ የመጨረሻው ዓላማችን እንደ እርስዋ መሉ በሙሉ ንፁሓን መሆን ነው’ ሲሉ የበዓሉ ትምህርት ኣቅርበው፣ ኣለኣዳም ኃጢኣት የተፀንሰች ድንግል ማርያም እንድትለምንልን ተማጥነዋል።

በመጨረሻም ሁሌ እንደሚደረገው በሓውልቱ በተኖረበት እግር ሥር የሚቀመጠውን የአበባ ጉንጉን በማረክ ኣስቀምጠው እዛው ተንበርክከው የግል ጸሎት ኣሳርግው ከኣንዳንድ ባለሥልጣናትና ምእመናን ተገናኝተው በሰላም ወደ መንበራቸው ተመልሰዋል።

ክቡራትና ክቡራን ኣድማጮቻችን የዚሁ በፕያሳ እስፓኛ ማለትም የእስፐይን አደባባይ በሚባለው በሮማ እምብርት የሚገኝ ትልቅ የማርያም ሓውልት ታሪክ ልናስታውሳችሁ፣ ይህ ኮሎና ደል ኢማኮላት በሚል መጠርያ ስም የሚታወቀው ሐውልት እ.ኤ.አ በታሕሣሥ 8 ቀን 1854 ዓም ብፁዕ ር.ሊ.ጳ ፕዮስ 9ኛ ለደንገጉት የማርያም ኣለ ኣዳም ኃጢኣት መፀነስ የሥርወ እምነት መታሰቢያ ምክንያት እንዲቆም የተደረገው የዳዊት ንጉሥ የኢሳይያስና የሕዝቅኤል ነቢያት እንዲሁም ሙሴ ስለ ማርያም ያሉትን ቃለ ትንቢት በአራት ማአዝን የያዘ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሐውልት የያዘ ነው።

ሥራው እንዲከናወን ሦስት ዓመት ኣስፈለገው፣ እ.ኤ.አ በታሕሣሥ 8 ቀን 1857 ዓም ር.ሊ.ጳ ሓውልቱን ባርከዋል፣ ር.ሊ.ጳ ፕዮስ 12ኛ በዓመታዊ ክብረ በዓሉ የአበባ ጉንጉን መላክ ጀምረዋል፣ ብፁዕ ር.ሊ.ጳ ዮሐንስ 23ኛ በ1958 ዓም በሰው ይላክ የነበረውን የአበባ ጉንጉን ገዛ ራሳቸው ሂደው ኣኖሩት፣ ከዛ በኋላ ጳውሎስ 6ኛ እንዲሁም ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ይህንን ልማድ ኣለማቋረጥ ኣዘወተሩት።








All the contents on this site are copyrighted ©.