2010-12-08 13:25:05

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ እንደ ማርያም በእግዚአብሔር ፈቃድ የታመኑ ትሁታን


በላቲን ሥርዓት ዛሬ በዓለ ጽንሰታ ለማርያም ማለትምንጽሕት ድንግል ማርያም፣ እርሱም ኵላዊነት ቤተ ክርስትያን ቅድስት ድንግል ማርያም አለ አዳም ሐጢአት መጸነስዋ የምታከብርበት ዓቢይ በዓል ሲሆን፣ ይህ አቢይ በዓል ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2006 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባሳረጉት ጸሎተ መልእከ እግዚአብሔር፣ RealAudioMP3 ቅድስት ድንግል ማርያም ሊደረስ የማይቻለው ለእግዚአብሔር መለኮታዊ ፈቃድ የምሉእ መልስ ማደሪያ መሆንዋ አለ ምክንያት አይደለም ቅዱስ ወንጌል ትህትናዋን በእጅጉ የሚያጎላው። ዳንተ አሊገሪ በማኅልየ መንግሥተ ሰማይ በሚል ድርሰቱ ድንግል እናት የልጅዋ ልጅ፣ ትሁት እና ከፍጥረት እጅግ የላቀች፣ ቋሚ የዘለዓለማዊ ምክረ ሰናይ ማረፊያ ብሎ ሲሰይማት አለ ምክንያት አይደለም ብለው፣ እግዚአብሔር በዚህች በርእርሱ ፊት ግርማ የተሞላች ሆና ባገኛት በማርያም ትህትና እጅግ ተመረከ፣ በማለት እንደገለጥዋት የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።

በፍጥረት ጅማሬ ዲያብሎስ ድል አድራጊ ተመስሎ ሲያበቃ ሆኖም ግን ከሴቲቱ በሚወለደው ልጅ እራሱ ይቀጠቀጣል፣ በዚህች ሴት ዘር አማካኝነት እግዚአብሔር ድል አድርገዋል፣ ከዚህች ሴት የተወለደው ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ በመሠዋት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጥንታዊው ፈታኙ ላይ ድል አድርገዋል፣ ለዚህም ነው የንጽህት ድንግል ማርያም ቅዱስ ምስል ከጥንት ጀምሮ በእግርዋ ዲያምብሎስን ስትረግጥ የሚያሳየው በማለት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ይኸንን ዓቢይ በዓል ምክንያት በማድረግ ባሳረጉት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ባቀረቡት ስብከት በማስረዳት፣ ንጽሕት ድንግል ማርያም እንደ እናት መቀበል ምንኛ ጸጋ ነው። ከደካማነታችን እና የክፋት መንፈስ ሴራ አማካኝነት በእለታዊ ኑሯችን ችግር እና ፈተና ሲያጋጥመን፣ እርሷን መጠጊያ ስናደርግ እና ወደ እርሷ ስንማጠን ልባንች ብርሃን እና መጽናናትን ይጎናጽፋል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ገልጦታል።

ሕይወቱን በእግዚአብሔር እጅ ሙሉ በሙሉ የሚተው የእግዚአብሔር አሻንጉሊት፣ ችክ ያለ ወይንም አሰልች ሰው ሳይሆን ነጻነትን የማያጣ ሰው ይሆናል፣ በእግዚአብሔር እጅ ሙሉ በሙሉ እራሱን የሚተው ሰው እውነተኛ ነጻነትን ይቀዳጃል፣ የነጻነት ጥልቅነት እና ኅያውነትን እና መልካምነትን ያጣጥማል።

ወደ እግዚአብሔር አቤት የሚል ትንሽ ሳይሆን ትልቅ ይሆናል፣ ምክንያቱን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁነውና ከእርሱ ጋር ታላቅ በመሆን መለኮታዊነትን በመላበስ በእውነት እራሱ ለመሆን ይበቃል። ሕይወቱን በእግዚአብሔር እጅ የሚያኖር ለሌሎች ቅርብ ይሆናል፣ በግላዊ መዳኑ ሳይመንን ልቡ የነቃ ርህሩህ የዋህ እና ክፍት ይሆናል ሲሉ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ለበዓለ ጽንሰታ ለማርያም ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት መግለጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.