2010-12-06 15:57:03

የኢራቅ ክርስትያኖች ሁኔታ


ቅዱስነታቸው በትናንትናው የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ ኣስተምህሮ እንዳመለከቱት የኢራቅ ክርስትያኖች እጅግ ኣሳሳቢ በሆነ ሁኔታ ነው የሚግኙት። ከሁሉም በላይ የሚያሳስበው ግን በዚሁ ስደት ሳቢያ ክርስትያኖች ለሕወታቸው ደኅንነት ሲሉ ኣገሩን ለቀው እየተሰደዱና ለችግር እየተዳረጉ ሲሆን የኣገሪቱ ቤተ ክርስትያን እየወደመች መሆንዋ ነው።

ለዚህ ችግር መፍትሔ ምን ይሆን ለሚለው ኣሳብ በኢራቅና በዮርዳኖስ የቅዱስ ኣባታችን ሐዋርያዊ እንደራሴ ወይም ኑንስዮ ብፁዕ አቡነ ጆርጅዮ ሊንግዋ በኢራቅ የሚገኙ ምእመናንና ቤተ ክህነትን የሚያጠቃልል ኣንድ ስብሰባ በማድረግ ሁኔታውን መግምገምና ኣገር ጥሎ መሄድን እንዴት ለማቆም እንዲቻል ጉባኤ ማካሄድ ያሻል ብለዋል። ብፁዕነታቸው ኣስተያየታቸውን በመቀጠል ባለፈው ግዜ ከለዳውያን ጳጳሳት ለሙስሊሙ ባለሥልጣኖች ባቀረቡት ኣብየቱታ ሃይማኖትን ኣሳበው በክርትያኖች ላይ የሚፈጸሙት አሰቃቂ ዓመጾች ግልፅ በሆነ መንገድ እንዲያወግዙ ኣሳስበዋል፣ ይህም የሃይማኖት ነፃነትን በማጥፋት ኣንሳ ቁጥር ያላቸውን ሃይማኖቶች ስለሚያጠቃ ነው፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዓመጸኞቹ ክርስትያኖችን ለማጥቃት የሚያቀርብዋቸው ምክንያቶችም የምስልምና ሃይማኖት ዓላማ እንዳልሆነ ኣበክረው እንዲያስታውቁ ኣደራ ብለው ነበር፣ ሲሉ ያላቸውን ኣሳብ ኣቅርበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢጣልያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ፍራንኮ ፍራቲኒ በኢራቅ በመገኘት ትናንትና ከኢራቅ ፕረሲደንት ኣል ማሊኪ ጋር ተገናኝተው ስለ ጉዳዩ በተወያዩበት ግዜ የኢራቅ መንግሥት ጉዳዩን ልዩ ትኵረት በመስጠት ፓርላመንታዊ ኮሚሽን አቍሞ ክርስትያኖችን የሚከላከል የፖሊስ ቡድን እንዳዘጋጀ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.