2010-12-06 15:56:06

ዓመፅና ኣለመቻቻል እንዲወገድ


በትናንትናው የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ ኣስተምህሮ ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ በአሁኑ ግዜ የሰው ልጅ መብትንና የሃማኖትና ኅሊና ነፃነትን በመጣስ ብዙ ስደተኞችንና ንፁሓን ዜጋዎችን በመሳደድ እስከ ሞት ኣደጋ የሚዳርጉትን ተግባሮች ኣውግዘዋል። ዓመፅና ኣለመቻቻል እንዲወገድም ጥሪ ኣቅርበዋል።

ቅዱስነታቸው ያተኰሩባቸው ሦስት ልዩ ነጥቦች በኢራቅ ላይ እየተካሄደ ያለው የክርስትያን ስደትና መሥዋዕትነት በግብፅ ያለው የሃይማኖት ግጭቶች እና በግብፅና በእስራኤል መሃከል ስደተኞችን ኣግተው ጅሆ በመያዝ የሚደረገው ኢሰብአዊ ተግባራት ወዲያውኑ እንዲቋረጡ ጥሪ ኣቅርበዋል።

በኢራቅ በተነሳው የክርስትያን ስደት በየጊዜው ብዙ ክርስትያኖች ለስደትና ለሞት እንዲዳረጉ ኣድርገዋ፣ ከትናንትና ወዲያም ሁለት ክርትያኖች ኣለምንም በደል ክርስትያን በመሆናቸው ብቻ ተገድለዋል። በግብፅ እየተካሄደ ያለው ፀረ ክርስትያን ስደትና ጭቆናም እየቀጠለ ነው።

የሰው ልጅን እንደ ማንኛው ቍሳቍስ ኣግተው በመያዝ የገንዘብ ክፍያ የሚጠይቁ በተለይም ስደተኞችን ማንም ሊረዳቸው በማይችልበት በሲና ምድረበዳ ጅሆ በመያዝ ወይም ይህን ያህል ክፈሉ ወይም ትገደላላቸው በማለት ኣለኣግባብ ብዙ ነፃ የማስለቀቅያ ክፍያ ገንዘብ እየጠየቁ ያሉ ነፍሰ ገዳዮች እንጂ ሌላ ስም ልትሰጣቸው የማትችል ሰዎች ብዙ ኤርትራውያን የሚገኙባቸው ስደተኞችን እያሰቃዩ መሆናቸው ሶሙኑን ልዩ ልዩ የመገናኛ ብዙኃን ኣውታሮች ገልጠዋል።

ቅዱስነታቸው ይህንን ሁሉ በማውገዝ እንዲህ ሲሉ ለፀሎትና ለነፃነት ጥሪ ኣቅርበዋል።

‘ለሁሉም የዓመፅ ሁኔታዎች የኣለመቻቻል ኑሮ በዓለም ስላለው አጠቃላይ ሥቃይ እንድትጸልዩ ጥሪ ኣቀርባለሁ፣ በኢየሱስ መምጣት ይህ ሁሉ ኣብቅቶ መጥናናት እርቅና ሰላም እንዲሰፍን እንጸልይ። ስለ ብዙ ኣስቸጋሪ ነገሮች ኣስባለሁ፣ በተለይ በኢራቅ ፀረ ክርስትያንና ፀረ ሙስሊሞች የሚካሄዱ ብዙ የሰው ሕይወት የቀስፉ የሽበራ ተግባሮች፣ በግብፅ ሃይማኖትን ሰበብ በማድረግ ብዙ ሕይወት ያጠፉና ብዙዎችን ያቆሰሉ ግጭቶች፣ በሕገ ወጥ ሰዎችን ከቦታ ወደ ቦታ የሚያዘዋውሩ የሰው ልጅ ነጋዴዎችና ነፍሰ ገዳዮች በተለይ በሲናይ ምድረበዳ ብዙ የኤርትራ ተወላጆችና ሌሎች ዜጎች ጅሆ በመያዝ እያሰቃዩ ያሉ እጅግ ኣሳስቦኛል። የሰው ልጅ መብት እንዲጠበቅና የሠለጠነ ኣብሮ የመኖር ዘዴ እንዲደረግ ኣደራ እላለሁ። ለጌታ የምናሳርገው ጸሎትና በዚሁ ትልቁ ሥቃይ ለሚገኙት ወገኖቻችን የምናሳየው ኣጋርነት ተስፋ ሊሆንዋቸው ይችላሉ። በማለት የምራቸውን ተናግረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.