2010-11-30 14:41:54

ኢጣልያ፦ 25ኛው ብሔራዊ የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ


እ.ኤ.አ. መስከረም 2011 ዓ.ም. በአንኮና ከተማ የኢጣልያ ቤተ ክርስትያን 25ኛው የቅዱስ ቍርባን ጉባኤ እንደምታካሂድ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ተገኝተው በሚሰጡት መሪ ቃል እንደሚጠናቀቅ የአንኮና እና ኦዚሞ ሜትሮፕሊታ ብፁዕ አቡነ ኤዶዋርዶ መኒከሊ በላቲንን ሥርዓት የመጀመሪያው እሁድ የምጽአት ዘመት መክፈቻ ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት ማሳወቃቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቤተ ክርስትያን በዘመነ ምጽአት በምትከተለው ሊጡርጊያ በታሪክ የአማኞችን ልብ እና ቀልብ ተገቢው መንገድ ለመለየት ይችል ዘንድ በተስፋ የአዳኝ ዳግመ ምጽአት እና ግልጸት ነቅቶ እንዲጠባበቅ ሕንጸት የምታቀርብበት ወቅት መሆኑ ብፁዕ አቡነ መኒከሊ በማብራራት፣ በቅዱስ ቁርባን ኅያው የሆነውን ክርስቶስን ማወቅ ቤተ ክርስትያን በማህበራዊ ሁኔታ እና በመንፈሳዊነት ረገድ ሁሉም ይኸንን የእምነት እውነት በመኖር ለጉባኤው ከወዲሁ እንዲዘጋጅ የኢጣሊያ ቤተ ክርስትያን ለሁሉም በይፋ ጥሪ አቅርባለች። በቅዱስ ቁርባን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅላዌ ኅያው እና የሚያስደንቅ ክብር የተሞላው በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ከመስከረም 3 ቀን እስከ መስከረም 11 ቀን 2011 ዓ.ም. የኢጣሊያ ቤተ ክርስትያን የምታካሄደው 25ኛው የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ፣ የዘመኑ ሰው የተጋረጠበት ሰቆቃ እና ባዶነት፣ ብቸኝነት እና ሥጋት በማዳመጥ፣ በቅዱስ ቁርባን ኅላዌው የተረጋገጠ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት መንገድ እና እውነት መሆኑ በመመስከር መሥዋዕት አድርጋ የምታቀርብበት ቅዱስ አጋጣሚ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም፣ ጉባኤው ለሚያምኑት ብቻ ሳይሆን በማወቀም ካለ ማወቅም ከእግዚአብሔር ምሥጢር ርቀው ለሚገኙት ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚያፈቅራቸው በክርስቶስ የተገለጠው እግዚአብሔር የሚያስፈራ ሳይሆን መሐሪ መሆኑ በመመስከር ይኽንን በሚገልጠው ማእድ እንዲሳተፉ ጥሪ የሚያቀርብ መሆኑ አብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.