2010-11-30 14:45:33

አልጀርስ፣ የአፍሪቃ ኅብረት ጠቅላይ ጉባኤ


የራዲዮ እና የተሌቪዥን ሥርጭት መስፋፋት በአፍሪቃ በሚል ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኰረ የአፍሪቃ ብሔራዊ የራዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ኅብረት የጠራው ጉባኤ በአልጀርስ ከተማ ቅዳሜ ጧት መጀመሩ ሲገለጥ፣ በዚህ በአፍሪቃ የሚገኙት የመንግሥት እና የግል የረዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እያሳተፈ ባለው ጉባኤ የኤውሮጳ የእስያ እና የላቲን አሜሪካ እና እንዲሁም ሌሎች ከምዕራብ ዓለም የተወጣጡ የቴሌቪዥን እና የረዲዮ ጣቢዎች ልዑካን ጭምር እየተሳተፉ መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል።

የቅድስት መንበር የዜና እና የኅትመት ጉዳይ ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ለጉባኤው ባስተላለፉት መልእክት፣ በቅርቡ በቫቲካን የካቶሊክ የመገናኛ ብዙኃን በዚህ የሥነ አኃዝ ምርምር እድገት በተፋጠነበት ዘመን በሚል ርእስ ሥር ተካሂዶ የነበረውን ዓውደ ጥናት በመጥቀስ፣ ቤተ ክርስትያን የመገናኛ ብዙኃን ዓለም ቀርባ እና በትኵረት እንደምትከታተለው እና የዚህ መሣሪያ ተጠቃሚ መሆንዋንም ጭምር ጠቅሰው፣ ይህ በሥነ አኃዝ ሥነ ምርምር ተሸኝቶ በማደግ ላይ ያለው የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት በተለያዩ አቢያተ ክርስያን በባህሎች በሕዝቦች እና በፖለቲካው ዓለም ውይይት እና ግኑኝነት እንዲኖር የሚያግዝ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያሉትን ሐሳብ አባ ሎምባርዲ መሠረት በማድረግ፣ የመገናኛ ብዙኃን ለዕደ ጥበባዊ እድገት እና ለሥነ አኃዝ እድገት ብቻ በማተኮር እና ዜናዎች በፍጥነት ለሁሉም ለማዳረስ እና በቅድሚያ ዜናውን ያሰራጨው እየተባለ ለሚደረገው ሽቅድድም በማተኮር የመገናኛ ብዙኃን ሰባአዊነት የተላበሱ እንዲሆኑ የሚለውን ተቀዳሚው ዓላማ ቸል እንደሚሉት በማስታወስ፣ በአፍሪቃ የመገናኛ ብዙኃን በክፍለ ዓለሟ የሰው ዘር ቤተሰብአዊነት ውህደት ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት መሣሪያ ሆኖ እንዲገኝ አደራ በማለት ያስተላለፉት መልእክት አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.