2010-11-30 14:46:41

ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፣ ዘገምታዊ የሥነ ሕይወት ለውጥ


በኢጣሊያ ሚላኖ ከተማ የካቶሊክ ሐኪሞች ማኅበር የባህል ጉዳይ ከሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ጋር በመተባበር በእምነት እና በምርምር መካከል በሥነ ዘገምታዊ ለውጥ እና በሥነ ሕይወት በፍጥረት እና በዘገምታዊ ለውጥ ዘንድ ያለው ግኑኝነት በሚል ርእስ ሥር በተካሄደው ዓውደ ጥናት የተሳተፉት፣ የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራኮ ራቫዚ በእምነት እና በምርምር ያለው ግኑኝነት ሁለቱም መድረኮች የሚከተሉት የምርምር መንገድ የተለያዩ ቢሆንም ቅሉ ጥናት የሚያካሂዱበት ተጨባጩ ጉዳይ የጋራ መሆኑ በማብራት፣ በሥነ ምርምር በፍልስፍና በቲዮሎጊያ ዘንድ ያለው ልዩነት እና ግኑኝነት በጥልቀት አስረድተዋል።

የሥነ ምርምር ዘርፎች በመከባበር አንዱ የሌላውን ተገቢው የምርምር ተገቢው ሥፍራ የራሱ ሳያደርግ እና የራሱ ቅኝ ግዛት ሳያደርግ ብሎም ይገባኛል ሳይል በሚያደርጉት የምርምር ጥናት ፍጥረት እርሱም መሆንን ለመረዳት እና ለመግለጥ ብሎም ያለውን ትርጉም ለመረዳት ያቀደ ከመሆኑ አንጻር መቀራረብ የተካኑ ናቸው ካሉ በኋላ ሥነ ዘግመታዊው የምርምር ጥናት አልቦ እግዚአብሔር ባህል የሚያጎላ ነው ብሎ በደፈናው ቅድመ ፍርድ የመስጠቱ አዝማሚያ መሠረት አማኝ ይኸንን የሥነ ምርምር ዘርፍ ከወዲሁ እንዲቀናቀነው የሚገፋፋው ባህል በጋራ በሥነ ባህላዊ መድረክ መዋጋት እና ስህተት መሆኑ በአመክንዮ የተደገፈ መልስ መስጠት የሁሉም ምሁራን እና የትምህርት ዘርፎች ተቀዳሚ ዓላማ መሆን አለበት ብለዋል። በመቀጠልም ይላሉ፣ በተለያዩ የሥነ ምርምር ዘርፎች የሚሰጠው መልስ የሥነ ኅልውና ማእከል በማድረግ ለሚደረገው ጥናት በተለያየ መልኵ የሚሰጥ ለአንዳዊ እና ጠቅላይ መልስ አስተዋጽዖ ያለው መሆኑ ገልጠው እያንዳንዱ የትምህርት ዘርፍ ወይንም የምርምር ዘርፍ ያለው የገዛ ራሱ ማለትም ሉአላዊ ገጽታው ማክበር ግድ እና ኃላፊነትም ነው ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፣ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛን በመጠቀስ፣ ዘገምታዊ ለውጥ በፍጥረት ዘንድ የተካተተ የመለኮታዊ ፍጥረት እቅድ ነው። ስለዚህ ሥነ ፍጥረት ዘገምታዊ ለውጥን አያገልም ካሉ በኋላ በእምነት እና በምርምር መካከል ያለው ውይይት በህሉም ዘንድ እየታወቀ እና ግንዛቤ እያገኘ መሆኑ ጠቅሰው፣ ሆኖም ሁለቱን ዘርፍ ለማራራቅ እና እንደማይገናኙ ለማድረግ በአክራሪነት መንፈስ የሚንጸባረቀው አመለካከት አጥጋቢ እንዳልሆነና እና አመክንዮ አልቦ ነው ብለዋል። ሰውን እና ተፈጥሮን ለመረዳት እምነት ወይንም ቲዮሎጊያ ለብቻው ምሉእ አይሆንም፣ በተመሳሳይ መልኩ ሥነ ምርምር ለብቻው በቂ አይደለም በማለት በሁለቱ ዘርፍ የተሟይነት ባህርይ እንዳለ ማብራራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.