2010-11-30 14:43:02

በቅድስት መንበር አዲስ የጃፓን ልዑከ መንግሥት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቅዳሜ በቅድስት መንበር የጃፓን ልኡከ መንግሥት እንዲሆኑ ከመንግሥታቸው የተላኩት ሪደካዙ ያማጉቺ ያቀረቡት የሹመት ደብዳቤ ተቀብለው ባሰሙት ንግግር፣ ዘንድሮ በመታሰብ ላይ ያለው የርሂሮሺማ እና ናጋሳኪ የአቶሚክ ቦምብ ድብደባ 65ኛው ዓመት አስታውሰው፣ ጃፓን የሰላም መሣሪያ ትሆን ዘንድ ጥሪ ሲያቀርቡ፣ በነዚህ ሁለት ከተሞች የተጣለው የአትኖሚክ ቦምብ ጥቃት ዓለማችን የጸረ ኒክሊዮር ጦር መሣሪያ እንዲፈታ ለሚደረገው ጥረት ምክንያታዊ ከማድረግ አልፎም ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት አግኝቶ በሁሉም አገሮች ዘንድ እንዲከበር የሚያነቃቃ ታሪካዊ እውነት ነው ብለዋል። በዚህ ረገድ ጃፓን በዓለም አቀፍ መድረክ አብነት በመሆን ለሰላም የምታደርገው ጥረት ለሁሉም ግልጽ ነው ካሉ በኋላ፣ የጃፓን ጸረ የኒክሊየር ጦር መሣሪያ ዓላማ ቅድስት መንበር በመደገፍ እና በማበረታታት መንግሥታት ለዚህ ዓላማ ይተጉ ዘንድ አበክራ እንደምታነቃቃ ቅዱስነታቸ በመጥቀስ ለጦር መሣሪያ ሽቅድድም የሚፈሰው የገንዘብ ሃብት ለልማት እና ለሰው ልጅ የተሟላ እድገት ማስተግብርያ ይውል ዘንድ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

በዓለማችን ሰላም እንዲረጋገጥ በመካከለኛው ምሥራቅ እና ሩቅ ምሥራቅ በተለይ ደግሞ በማደግ ላይ በሚገኙት አገሮች የዴሞክራሲ ሥርዓት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ መስፋፋት ጃፓን የምትከተለው የፖለቲካ ሥርዓት አብነት መሆኑ ቅዱስነታቸው በመጥቀስ፣ በቅድስት መንበር እና በጃፓን መካከል ያለው ግኑኝነት 60ኛ ዓመቱን እንዳገባደደ ዘክረው፣ በዚያች አገር የሃይማኖት እና የኅሊና ነጻነት ጥበቃ ምክንያት በጃፓን ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በማኅበራዊ እና በባህላዊ መስክ ጭምር ለምትሰጠው አስተዋጽኦ ድጋፍ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.