2010-11-26 14:06:51

የክርስትያን ቤተሰብ ጥሪ


የቤተሰብ ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ቤተሰብ የሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተቀዳሚ ልዩ ተወናያን በሚል ርእስ ሥር የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሥልጣናዊ ትምህርት ፈር በመከተል እንዲወያይ የጠራው ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ ትላትና ስብሰባው ያዘጋጀው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኤኒዮ አንቶነሊ ባሰሙት ንግግር በይፋ መጀመሩ የቅድስት RealAudioMP3 መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ይህ እስከ ነገ የሚቀጥለው ዓለም አቀፍ ስብሰባ የሚወለድ ሕይወት በሚል ርእሰ ጉዳይ ሥር በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሕይወት ባህል ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት እንዲከበር የሚያነቃቃ በሚመሩት የዘመ ምጽአት ዋዜማ ቀዳሜ ጸሎተ ሠርክ እንደሚፈጸም ብፁዕ ካርዲናል አንቶነሊ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።

ይህ ከአምስቱ ክፍለ ዓለም የተወጣጡ 187 ተጋባእያን እያሳተፈ ያለው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ቤተሰብ ኅብረተሰብ እና የእያንዳንዱ የሰው ልጅ ልብ እንዲለወጥ የሚያደርግ እምነት በማስተላለፈ እና በአስፍሆተ ወንጌል ግብረ ተልእኮ አቢይ ኃላፊነት ያለው በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተቀዳሚ ልዩ ተወናያን መሆኑ በጥልቀት እንደሚወያይ ሲገለጥ፣ ስብሰባው ቋሚ ልምድ እና የምስክርነት ግኑኝነት የሚል እቅድ ማእከል ያደረገ የቤተሰብ ሐዋርያዊ ግብር ኖልዎ እንዲመሠረት ብፁዕ ካርዲናል አንቶነሊ ጉባኤው በንግግር ሲከፍቱ ባሰሙት ንግግር በመግለጥ፣ የእምነት እና የእሰፍሆተ ወንጌል ልምድ እና ስለ ጉዳይ በተመለከተ ምስክርነት ጭምር ለመለዋወጥ የሚያግዝ እቅድ እንደሚወጠንም ጠቅሰው፣ ቤተሰብ የሰው ልጅ ነፃነት ትክክለኛው አገላለጥ እና እኗኗር የሚያበስር፣ ይኽም የሕይወት ባህል በማስከበር የሚረጋገጥ መሆኑ የሚመሰከርበት የኅብርሰብ ልብ ነው ብለዋል።

ቤተሰብ የክርስትና እምነት መልካም አብነት ብቻ ሳይሆን ምሥጢረ ቤተ ክርስትያናዊነት የሚገለጥበት እና የእግዚአብሔር መለኮታዊ ጸጋ የሚስተናገድበት የሚታቀብበት የሚከበርበት የክርስትናው ፍቅር መግለጫ ሳይሆን የክርስቶስ ፍቅር የሚስተናገድበት የሚኖርበት ለሌሎች የሚበሰርበት የተቀደሰ ሥፍራ ነው በማለት፣ እያንዳንዱ ቤተሰብ ይኸንን ጥሪውን በሚገባ ለመኖር እና ለዚህ ልዑል ጥሪ የተገባ እንዲሆን የክርስትናው እምነት በማበሰሩ ረገድ ያለው ውበት እና የክርስትናው ውበት በመኖር የሚመስክር እውነት፣ ቅድስና ማእከል ያደረገ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማጎልበት ይጠበቅበታል፣ ስለዚህ ቤተሰብ ለንግለንጋ ወይንም ለብ ያለ የክርስትና ሕይወት የሚኖርበት፣ አነስተኛ እና የተገባውን ግብረ ገብ ብቻ የሚኖር የቅድስና ሕይወት የማይተኮርበት የቅድስትና ዓላማ ግብ የማያደርግ መሆን የለበትም ብለዋል። የእግዚአብሔር ምህረት ማእከል ያደረገ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የሚገለጥበት ለመወያየት ሌላውን ለመረዳት እና ለመቀበል ክፍት ልብ ያለው፣ የተሟላ የሰብአዊ እድገት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ የቤተሰብ የማኅበረሰብ መልካምነት የሚገለጥበት እና ይኸንን ሁሉ በማኅበራዊ ሕይወት በተጨባጭ ተግባር የሚያበሥር መሆን አለበት ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ይኸንን ጉባኤ በይፋ ለማስጀመር ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የአምልኮ እና የቅዱሳት ምሥጢራት ሥርዓት የሚንከባከብ ቅዱስ ማህበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ካኛዛረስ ልዮቨራ መሆናቸው ሲገለጥ፣ ብፁዕነታቸው ቅዳሴውን መርተው ባሰሙት ስብከት፣ ቤተሰብ አንድነቱን እና ቤተሰብአዊ ምሥጢርነቱን በቅዳሴ ሥርዓት በመሳተፍ እንደሚገለጠው እና ቢያስን በሳምንት አንዴ እርሱም ዕለተ ሰንበት በማክበር እና በቅዳሴ ሥርዓት የመሳተፍ ክርትያናዊ ኃላፊነት እና ጥሪ የተቀበለ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.