2010-11-26 14:10:53

የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ


ባለፈው ሰኞ የውህደት አንግሊካዊት ቤት ክርስትያን ሲኖዶስ የቤተ ክስትያንዋ መንፈሳዊ የበላይ መሪ የካንተርበርይ ሊቅ ጳጳስ ሮዋን ዊሊያምስ እና የታላቅዋ ብሪጣንያ ንግሥት ኤሊዛቤጥ ባሰሙት ንግግር በይፋ መጀመሩ ሲገለጥ፣ RealAudioMP3 ይህ በመካሄድ ላይ ያለው የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ ለአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን መከፋፈል አቢይ ምክንያት ከሆኑት ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ የሰዶም ጾታዊ ስሜት ባላቸው ሰዎች መካከል የጋብቻ ፈቃድ እና የዚህ ዓይነት ጾታዊ ስሜት ላላቸው ሰዎች የክህነት ማዕርግ መስጠት በሚሉት ርእሰ ጉዳዮች በመወያየት ለሁሉም ለታላቅዋ ብሪጣኒያ አንግሊካውያን ቤተ ክርስትያን ሰበካዎች ድምጽ እንዲሰጡበት ጥያቄው እንዲቀርብ በማድረግ ከግምሽ በላይ የቤተ ክርስትያንዋ ሰበካዎች ከተቀበሉት ይህ የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን እ.ኤ.አ. በ 2012 ዓ.ም. ወሳኝ ድምጽ በመሰጠት እንዲሚያጸድቀውም ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በሜክሲኮ የምትገኘው አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን እ.ኤ.አ. በ 2004 ዓ.ም. አንድ ካህን በግልጽ ሶዶማዊ ጾታዊ ስሜቱን ቢያሳወቅም የጵጵስና ማእርግ በመስጠት በመላ አንግሊካዊት ቤት ክርስትያን አቢይ ጥያቄ እንዲሆን ከማድረግ አልፎ በቤተ ክርስትያንዋ ለመከፋፈል ምክንያት ሆኖ መገኘቱ የሚዘከር ሲሆን፣ ይኸንን መክፈፋፈል ለመጠገን የሚያግዝ የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክስትያን ሲኖዶስ ስለ ጉዳዩ በማስመልከትም የአንግሊካን የውህደት ቃል ኪዳን ሰነድ ማጽደቁ የሚዘከር ሲሆን ሆንም ግን ይሕ የቃል ኪዳኑ ሰነድ አሁንም አከራካሪ እየሆነ ቢሆንም ዳግም ውይይት እንደሚደረግበት ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.