2010-11-26 14:08:37

ቃለ እግዚአብሔር በሊጡርጊያ እና በእለታዊ ኑሮ


የኢጣሊያ ብሔራዊ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሥር የሚታቀፈው የፒዮሞንተ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. ያጸደቀው የመጽሓፍ ቅዱስ ኅትመት በመጠቀም በየዕለቱ RealAudioMP3 በሚያርገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የሚነበበው ወንጌል ያጠቃለለ በፓዶቫ መሳጀሮ ማተሚያ ቤት የታተመው አዲስ የቅዳሴ መጽሓፍ ከትላትና በስትያ እዚህ ራዲዮ ቫቲካን በሚገኘው የጉለልሞ አዳራሽ በይፋ መቅረቡ ተገለጠ።

የእግዚአብሔር ቃል በቅዳሴ ሥነ ስርዓት ለመኖር ብቻ ሳይሆን እርሱን በቃሉ አማካኝነት ለማየት ቅዱስ መጽሓፍ እንደሚለው የእግዚአብሔር ሕዝብ ቃለ እግዚአብሔር አየ፣ ነቢይ የእግዚአብሔርን ቃል አየ፣ የሚለውን እውነት እንዲከተል እና እንዲኖር የሚያግዝ መሆኑ ሲገለጥ፣፣ የእግዚአብሔር ቃል በቅዳሴ ሥነ ስርዓት ማዳመጥ ብቻ ሳይሆን ማዳመጥ እና ማየትን በማገናኘት የሚደመጥ እና የሚታይ ቃል ሆኖ እንዲኖር የሚያግዝ የሊጡርጊያ መጽሓፍ መሆኑ የቦዜ መናንያን ማኅበር አበ እምኒየት ወንድም ኤንዞ ቢያንኪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ቅዱስ መጽሓፍ ከፍቶ ቃለ እግዚአብሔር ማንበብ ማዳመጥ ማለት ሲሆን ይኽ ደግሞ እግዚአብሔርን ማየት ጭምር እንደሚያሰማ ነው ካሉ በኋላ፣ የቤተ ክርስትያን ቅዱሳት ጉባኤ ያጎላው ሐሳብ እና ተግባር መሆኑ አብራርተው፣ እግዚአብሔር በቃሉ ኅላዌው በመግለጥ በዘመናት እንደተገለጠ ሁሉ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሁለት ሺሕኛው ቅዱስ አመት በቅድስ በር በማለፍ ሲከፈቱ ከፍ በማድረግ ያነሱት የእግዚአብሔር ቃል ነው። በመቀጠለም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ “የጌታ ቃል በቤተ ክርስትያን ሕይወት እና ተልእኮ በሚል ርእስ ሥር እንዲወያይ የጠሩት የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ 12ኛ ጠቅላይ መደበኛ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 5 ቀን እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. እዚህ በቫቲካን የተካሄደውን በመዘከር፣ የዚህ ጥልቅ እና ሰፊ ቅዱስ ሲኖዶስ የተወያየባቸው፣ ሀሳብ ለሀሳብ የተለዋወጠባቸው፣ በጠቅላላ ከጉባኤው የፈለቀ የውይይት ህሳብ በቅደም ተከተል የጌታ ቃል በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን የደረሱት ድህረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ህዳር 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በይፋ ለንባብ የበቃውን ጠቅሰው፣ ቅዱስ አባታችን የቃል እግዚአብሔር ቅዱስ ምሥጢርነቱን በመግለጥ እና በማብራራት፣ ይኽ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል በክርስትያን ሕይወት ያለው ማእከላዊ ሥፍራ የሚመሰክር ነው ብለዋል።

የቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ምዕዳን “በግል ሕይወት እና በቤተ ክርስትያን ሕይወት የቃለ እግዚአብሔር ማእከልነት ዳግም ተገቢ ሥፍራ እንዲያገኝ እና ለመላ የሰው ልጅ ድህነት የማብሠሩ ዓላማ አስቸኳይ እና ያለው ውበት፣ ሞትን አሸንፎ ለተነሣው ጸኑ እና ታማኝ ምስክር ሆኖ መገኘት፣ ይኽ ደግሞ ዘለዓለማዊው ቃል ሥጋ የለበሰው እግዚአብሔር የክርስትና ልዩ መግለጫ እና መለያ ማብሰር በሚለው አጭር እና ጥልቅ ሀሳብ ሥር ለማጠቃለለ የሚቻል መሆኑ ያብራሩት ሐሳብ የሚያስተጋባ መጽሓፈ ግጻዌ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልድ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.