2010-11-20 14:57:41

የሰብአዊ ክብር ማእከል ያደረገ መፍትሔ


የገዓዝያን ጉዳይ የሚንከባከበው ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ድርገት ከትላትና በስትያ ሥራው በይፋ ለማጀመር ከመላ ዓለም የተወጣጡ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ልኡካን በማሳተፍ እስከ ነገ የሚቀጥል ስብሰባ በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ ሲገለጥ፣ የሰው ልጅ ክብር ዳግም ለማጎናጸፍ ለውጥ እና ኅዳሴ ለማነቃቃት በሚል መርህ ቃል ተሸኝቶ በመካሄድ ላይ ያለው ስብሰባ በዚህ በምንኖርበት ዘመን RealAudioMP3 የሰዎች ከቦታ ቦታ መዘዋወር ማኅበረሰብአዊ ክስተት የሚያቀርበው ጋሬጣ ለማሸነፍ ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ያቀደ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ይህ ልክ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳኣት ፒዮስ 12ኛ መልካም ፈቃድ እና ውሳኔ የተቋቋመው የገዓዝያን ጉዳይ የሚንከባከበው ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ድርገት 60ኛ ዓመት ለማክበር በመዘጋጀት ላይ ሲሆን፣ ስለ ጉዳይ በማስመልከት በጀነቭ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ አስከባሪ ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ቶማሲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በአሁኑ ወቅት ይላሉ የተባበሩት መንግሥታት መግለጫ በመጥቀስ 214 ሚሊዮን ሕዝብ ከትውልድ አገር ርቆ በሌሎች አገሮች ተሰዶ የሚኖር እና የሚሰራ መሆኑ ገልጠው፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለተፈናቃዮች ተገቢ መጠለያ ለመስጠት ጥረት መደረጉ ታሪክ ጠቀስ አብነት በማቅረብ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለስደተኞች እና ተፈናቃዮች የሚቀርበው እንክብካቤ የሰብአዊ ክብር ማእከል ያደረገ መሆን አለበት፣ ይህ እንዲሆን መንግሥታት ለዚህ ዓላማ ማስተባበር እና ማነቃቃት ግድ ነው። ለስደተኛ ተገቢ እንክብካቤ መስጠተ አጅግ አስፈላጊ ነው ሆኖም ግን ለስደት የሚዳርገው ሰብአዊ፣ ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ሃይማኖታዊ ወዘተ የመሳሰሉት ችግሮች መፍትሔ የማፈላለጉ ጥረት ተቀዳሚ ዓላማ መሆን አለበት።

ስደተኞች በተስተናገዱበት አገር ያላቸው እውቀት እና ሙያዊ ብቃት መሠረት በሥራው ዓለም በማህበራዊ ሕይወት እና በጠቅላላ በአገር ጉዳይ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ብሎም በትውልድ አገሮቻቸው ለቀሩት የቤተሰብ አባላት ከዘርፈ ብዙ ችግሮች ለማላቀቅ የሚያቀርቡት ደገፍ በቀላል የሚገመት አይደለም። ሆኖም ይኸንን የስደተኞች እምቅ ኃይል ሙሉ በሙሉ እግብር ላይ ይውል ዘንድ አዲስ እቅድ መቀየስ እጅግ አስፈላጊ ነው። የኤውሮጳ ኤኮኖሚ የሰው ኃይል አቀርቦት ሲጠይቅ፣ በሌላው ረገድ የስደተኛው ልምድ ባህል መለያ ለሚስተናገዱበት አገር ላለው ባህላዊ መለያ ሥጋት አድርገው የሚመለከቱት አካላት የሚፈጥሩት ማኅበራዊ ፍርሃት አሳሳቢ ነው። ስለዚህ እነዚህን ሁለቱ ጥያቄዎችን በማጣመር ተገቢ ምላሽ መስጠት ግድ ነው። ስደተኛ ኃብት ነው፣ መንግሥታት ይኽ ኃብት በተገባ መድረክ እግብር ላይ ይውል ዘንድ ጥበብ የተካነው የስደተኛ ማስተዳዳሪያ ደንብ በማቅረብ ይመሩት ዘንድ አስፈላጊ ነው። ስደተኛው እና አስተናጋጅ አገር ተገናኝተው መወያየት መቻል አለባቸው፣ ስደተኛው ከተስተናገደበት አገር ጋር ለመተዋወቅ የሚያግዘው እድል መፍጠር እና ስደተኛው የተስተናገደበት አገር ልምድ እና ባህላዊ ክብር ማክበር ይጠበቅበታል በዚሁ ጉዳይ ቤተ ክርስትያን የምትሰጠው አስተዋጽኦ ተጨባጭ እና የተሟላ መሆኑ ለማንም የተሰወረ እንዳልሆነ በማስረዳት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.