2010-11-17 15:07:12

የካቶሊክ እና የምስልምና ሃይማኖት የጋራ ውይይት


እ.ኤ.አ. ከህዳር 9 ቀን እስከ ህዳር 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢራን ርእሰ ከተማ ተሄራን የአገሪቱ በባህል እና የምስልምና ግኑኝነት ጉዳይ ሥር የሚመራው በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የሚደረገው የጋራ ውይይት የሚንከባከበው ማእከል እና ከተለያዩ ሃይማኖትች ጋር የሚደረገው የጋራው ውይይት የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የካቶሊክ እና RealAudioMP3 የምስልምና ሃይምኖት የጋራ ውይይት በተለያዩ ባህሎች እና የምስልምና ሃይማኖት ግኑኝነት ጉዳይ ሊቀ መንበር ዶክተር ሞሃማድ ባቀር ክሆራምሻድ እና ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚደረገው ውይይት የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራን በጋራ ሊቀመንበርነት ተመርቶ መካሄዱ የሚዘከር ሲሆን፣ ከተካሄደው የጋራው ውይይት ፍጻሜ፣ ጉባኤው አማኞች እና ማኅበረሰብ ሃይማኖት በእግዚአብሔር ላይ ባላቸው እምነት መሠረት በኅብረተሰብ ዘንድ ከሌሎች ዜጎች ጋር በእኩልነት ደረጃ ዓይነተኛ ሚና አላቸው ከሚል ሃሳብ በመንደርደር ባወጣው የጋራ መገልጫ፣ ሃይማኖት በባህርዩ ማኅበራዊ አድማስ ያለው በመሆኑ ይኸንን የሃይማኖት ውስጣዊ አድማስ፣ መንግሥታት የማክበር ግዴታ አለባቸው፣ ስለዚህ ለማኅበራዊ ጥቅም ሲባል ሃይማኖት የግል ወይንም በግል ሕይወት የሚገለጥ እና የሚኖር ገለልተኛ ማድረግ እንደማይገባ በስፋት ያብራራል።

የሁሉም ሃይማኖት አማኞች በእምነት እና በሃይማኖት መካከል ያለው ጽኑ ግኑኝነት መሠረት በማድረግ የጋራ ጥቅም በማፈላለጉ ረገድ እንዲተባበሩ መጠራታቸው የተካሄደው የጋራው ውይይት ፍጻሜ ባቀረበው የጋራ ማጠቃለያ ሰነድ በማመልከት፣ በዚህ አገባብ እና ይዞታ መሠረት ክርስትያኖች እና ሙስሊሞች እንዲሁም የሌሎች ሃይማኖት አማኞች እና መልካም ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ወቅቱ የሚያቀርበው ፈተና የግብረ ገብ፣ የፍትሕ እና የሰላም እሴቶችን በማነቃቃት ብሎም ቤተሰብ፣ አካባቢ እና የተፈጥሮ ሃብት ለመከላከል በመተባበር ተገቢ ምላሽ መሰጠት አስፈላጊ መሆኑ ተብራርቶ ይገኛበታል።

በተጨማሪም የጋራው ውይይት ያረቀቀው የጋራው ሰነድ፣ እምነት በባህርዩ ነጻነትን የሚሻ እና የሃይማኖት ነጻነት በሰብአዊ ክብር ዘንድ የተጠቃለለ ከመሆኑም አልፎ በግልም ሆነ በማኅበራዊ ድርጅቶች እና መንግሥታት ጭምር መከበር ያለበት እውነት ነው። ስለዚህ ይኸንን መሠረታዊ እና ይፋዊ መመሪያ የእያንዳንዱ ኅብረተሰብ ከሰብአዊ ክብር ጋር የማይጻረረው ታሪካዊ እና ባህላዊ ገጽታውን እና ተመክሮ ግምት የሚሰጥ መሆን አለበት። ለወጣት የኅብረተሰብ ክፍል የሚሰጠው ትምህርት እና ሕንጸት እውነትን በመሻት በመንፈሳዊ እሴቶች እና ኅሊናን ማነቃቃት በሚለው ዓላማ ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት በጋራው ሰነድ ተሰምሮበት ይገኛል።

በመጨረሻም ተጋባእያኑ በተካሄደው የውይይት መድረክ በሁሉም ሃይማኖቶች መካከል ያለው ተምሳይነት እና ሕጋዊ ልዩነት እውቅና በመስጠት፣ በሁሉም ዘንድ መከበር እንዳለበት በመግለጥ የወዳጅነት መንፈስ የታየበት የጋራው ውይይት ከመሆኑም ባሻገር የዚህ ዓይነት በቅንነት ላይ የጸና ፍርያማ የጋራ ውይይት መቀጠል ያለበት አስፈላጊ መሆኑ በማብራራት ይህ በቴሄራን የተካሄደው ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ የጋራው ውይይት እ.ኤ.አ. ከ 1994 ዓ.ም. አንድ ብሎ ከጀመረበት እና ዘንድሮ እ.ኤ.አ. ከ ከህዳር 9 ቀን እስከ ህዳር 11 ቀን ያካሄደው የጋራው ውይይት ሥራ በእንግሊዝኛ እና በፐርሲያን ቋንቋ ታትሞ ለንባብ እንደሚቀርብ ጉባኤው በመስማማት፣ ቀጣዩ ግኑኝነት ከሁለት ዓመት በኋላ በሮማ እንዲከናወን እና ለዚህ የሮማው ግኑኝነት ማዘጋጃ ቅድመ ግኑኝነት ለማከናወን ጉባኤው እንደተስማማበት ተመልክቶ ይገኛል።








All the contents on this site are copyrighted ©.