2010-11-17 15:05:51

ር.ሊ.ጳ.፣ ቤተ ክርስትያን እና ወቅታዊ ትእምርት


እ.ኤ.አ. ህዳር 23 ቀን 2010 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ ልክ እራት ሰዓት ተኩል በቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ሕንጻ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከጋዜጠኛ ፒተር ሲዋልድ ለቀረበላቸው ቃለ መጥይቅ የሰጡት መልስ አዘል የዓለም ብርሃን፣ ር.ሊ.ጳ.፣ ቤተ ክርስትያን እና ጊዜ የሚያቀረበው ጥያቄ በተሰኘ ርእስ ሥር በቫቲካን ማተሚያ ቤተ ታትሞ ለንባብ RealAudioMP3 እንደሚቀርብ የቅድስቲ መንበር መግለጫ አስታወቀ።

መጽሐፉን ለንባብ ለማቅረብ በሚደረገው ውይይት ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ ጋዜጠኛ ልዊጂ አካቶሊክ ንግግር እንደሚያሰሙ ሲገለጥ፣ ቃለ መጠይቁ በማቅረብ ቅዱስ አባታችን የሰጡት መልስ ቅድም ተከተል በማስያዝ መጽሐፉን የደረሱት ጋዜጠኛ ዶክተር ፒተር ሲዋልድ የቫቲካን ማተሚያ ቤተ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ጁዘፐ ኮስታ እንደሚሳተፉም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.