2010-11-17 15:08:35

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ለሶስት ሺሕኛው ዘመን አቅጣጫ ጠቋሚ ነው


በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ የሥርወ እምነት ቲሊዮሊያ መምህር የቲሊዮሎግያ ሊቅ የእየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ዳሪኡስዝ ኮዋልችዝይክ ተመርቶ በቫቲካን ረዲዮ ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ማእከል በማድረግ የተጀመረው አዲስ RealAudioMP3 ሥርጭት፣ ትላትና የቤተ ክርስትያን ኅዳሴ በተመለከተ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ያመላከታቸው መንገዶች እና ነጥቦች ላይ በማተኮር ባቀረቡት ሓተታ፣ ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቤተ ክርስትያን ኅዳሴ ዘወትር አስፈላጊ ነው፣ ሆኖም ኅዳሴው ቀጣይነት ያለው የቤተ ክርስትያን ባህርይ በማክበር መከናወን እንዳለበት እና ቤተ ክርስትያን እንደ አንድ አካል እራስዋን ሳትለውጥ መለያዋን በማቀብ ተጓዥ የሕዝበ እግዚአብሔር ጉባኤ በመሆናዋም ከጊዜ ጋር የምታድግ እና የምትራመድ መሆን አለባት ያሉትን በመጥቀስ ሲያብራሩ፣ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ 23ኛ የእምነት ኅዳሴ የሚል ቃል በመጠቀም ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ እንዲካሄድ ጥሪ ሲያቀርቡ፣ የሲኖዶስ አበው ከመካከለኛው ክፍለ ዘመን ጋር ከተያያዘው አስተሳሰብ እና ፍልስፍና አቀራረብ ተከታይነት አጥር ወጣ በማለት እና አዲስ የነጻነት አመለካከት በማስከተል ጭምር፣ ይኽ አቢይ ጥንቃቄ የሚያሻው ጥሪ በጥልቅ በማጤን ለመጋፈጥ የተገናኙበት ቅዱስ ሲኖዶስ እንደነበርም ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ቀርበው የሚያውቁት የእምነት እና የቤተ ክርስትያን ገጠመኝ ነው ብለዋል።

ቤተ ክርስትያንን ለማደስ ይኽም ቤተ ክርስትያን ሁሌ ኅዳሴ ያሻታል የሚለውን ቃል በማስከተል፣ የቤተ ክርስትያን ኅዳሴው በምን ላይ የጸና ምንን የሚመለከት መሆን አለበት፣ እ.ኤ.አ. በ 1950 ዓ.ም. አባ ኮንጋር እውነተኛ እና ሐሰተኛ የቤተ ክርስትያን ኅዳሴ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሓፍ፣ ኅዳሴ የሚባለው ሁሉ አወንታዊ ውጤት አለው ማለት እንዳልሆነ ያብራራሉ። ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ 23ኛ በበኵላቸውም ለሁለተኛውን የቫቲካን ጉባኤ መክፈቻ ባሰሙት ንግግር፣ እርሱም አጠረ ባለ እና ጥልቅ በሆነ አገላለጥ ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 13 ቁጥር 52 “እንግዲያውስ የመንግሥተ ሰማይን ምሥጢር ጠንቅቆ የሚያውቅ የሕግ ምምህር ከመዝገብ አዲስ የሆነውንና አሮጌ የሆነውን እንደሚያወጣ ባለቤት ነው” የሚለውን የክርስቶስ ቃል የሚያስታውስ ነው። ቤተ ክርስትያን የእምነት ማኅደር/ማደርያ ነች የሚለው ጥንታዊው የሥርወ እምነት ይዞታ እና የተቀበለችው ኃላፊነት ማዋቀር የተሰኙት ሁለተ የተለያዩ ርእሶች ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ መሆኑ አባ ኮዋልችዝይክ ባቀረቡት የራዲዮ ሥርጭት በማብራራት፣ ስለዚህ መሻሻል ያለበት መቀየር ባለበት እና መቀየረ መለወጥ በሌለበት መካከል የተስተካከለ እና ሚዛኑ የጠበቀ ግኑኝነ ላይ የጸና አመለካከት መከተል አለበት። መለወጥ ያለበት እና መታቀብ ያለበት ለይቶ ማወቅ ለኅዳሴ ሂደት አስፈላጊ እና ወሳኝ መሆኑ አባ ኮንጋር በጻፉት መጽሓፍ ያብራራሉ። ወንጌላዊ ሥር ነቀል እና ኅዳሴ፣ ወንጌላዊ ተጨባጭነት እና ይኸንን ወንጌላዊነት ቤተ ክርስትያን ለምትኖርበት ዓለም ለመናገር ለመምስከር የምትጠቀምበት መሣሪያ ከወቅቱ ጋር የሚሄድ መሆን እንዳለበት የሚያመለክት ሐሳብ ነው። ስለዚህ ቤተ ክርስትያን ላስመሳይነተ አደጋ እንዳትጋለጥ አቢይ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ኅዳሴ ለማረጋገጥ የተደረገው እና በመደረግ ላይ ያለው ጥርት አመርቂ ውጤት እያስገኘ ነው። ሆኖም ግን ብዙዎች ኅዳሴ የሚለውን ቃል ተመሳስሎ እና ለማደር የሚለው ዓይነት መኖር በሚለው ሐሳብ ሥር የተሳሳተ መንገድ መከተላቸው አባ ኮዋልችዝይክ ብማብራራት፣ ይህ ደግሞ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንዳሉት እምነት በውኃ ማጥለቅለቅ ይሆናል፣ ስለዚህ ኅዳሴ ተመቻችቶ የካቶሊክ ሃይማኖት ቀለል አድርጎ ማቅረብ ማለት ሳይሆን፣ የካቶሊካ እምነት ዳግም እንዴት መኖር አለበት ከሚለው ጥያቄ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.