2010-11-16 14:16:15

የሱዳን ብፁዓን ጳጳሳት ጥሪ


እ.ኤ.አ. ጥር 9 ቀን 2011 ዓ.ም. የሱዳን የውስጠ ግጭት ሰላማዊ መፍትሔ ያስገኛል ተብሎ የሚጠበቀው ስለ ደቡብ ሱዳይ የመጪው እድል የሚያረጋገጠው ሕዝበ ውሳኔ ማእከል በማድረግ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት RealAudioMP3 ምክር ቤት በሩምቤክ ከተማ የመላ አፍሪቃ እና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳታ ምክር ቤት የምስራቅ አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ልኡካን ያሳተፈ እ.ኤ.አ. ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ.ም. የጀመረ ጉባኤ ትላትና ማጠናቀቁ ለማወቅ ሲቻል። ይህ በክልሉ በሚገኘው በቅዱስ ዳኒኤል ኮምቢኒ ተቋም የመላ አፍሪቃ እና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳትይ ምር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐንጎ ተመርቶ ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ተጀምሮ እ.ኤ.አ. እስከ ህዳር 15 ቀን 2010 የተካሄደው ስብሰባ እ.ኤ.አ. በ 2005 ዓ.ም. በሱዳን ሰላም ለማረጋገጥ የተደረሰው የስምምነት ሰነድ በሙላት እንዲከበር ያሳሰበ መሆኑ ተገልጠዋል።

በሌላው ረገድ ሕዝበ ውሳኔ የሚያስገኘው ውጤት ለሰላም እንጂ ለግጭት መንሳኤ እንዳይሆን ብፁዓን ጳጳሳት በመወያየት በሱዳን የተሟላ ሰላም እና ብልጽግና እንዲረጋገጥ የሕዝብ ውሳኔ ማክበር የሁሉም ኃላፊነት መሆኑ ጠለቅ ባለ መልኵ አለ ልዩነት ለሁሉም ለማስረዳት ቤተ ክርስትያን እና መልካም ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ያለባቸውን ኃላፊነት የሚያስገነዝብ እና የሚገልጥ መሆኑ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ስለ ተካሄደው ስብሰባ በማስመልከት የሩምበክ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቸሳረ ማዞላሪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የሱዳን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በመላ አፍሪቃ እና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳታ ምክር ቤት እና በምስራቅ አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ተደገፎ መከናወኑ በመጥቀስ፣ የሚከናወነው ሕዝበ ውሳኔ በሱዳን ብቻ ሳይሆን በሱዳን በምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ላይ ጭምር ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል ገልጠው። ወቅታዊው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አወቃቀሩ ላይ ለውጥ ሊያስከትል የሚችል ቢሆንም ቅሉ ቤተ ርክስትያን፣ አንዲት እና ኵላዊነት ናት። የሕዝብ ውሳኔ የሚያረጋግጠው ውጤት መከበር እንዳለበት ብፁዓን ጳጳሳት ካለ መታከት ጥሪ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ አብራርተው የሰጡትን ቃል አምልልስ ደምድመዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ሊቀ ጳጳሳት የኢትዮጵያና ኤርትራ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ሊቀ መንበር የመላ አፍሪቃ እና ማዳጋስካር ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አባል ብፁዕ ኣቡነ ብርሃነ የሱስ ሱራፊኤል፣ በሱዳን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጥሪ መሠረት በሩምበክ ጉባኤ መሳተፋቸው ገልጠው፣ ወቅቱ ለሱዳን የመጪው እድል ወሳኝ በመሆኑ ቤተ ክርስትያን እቅዱ በጸሎት እና ሕዝብን በማነጽ ሚና ለአገሪቱ ሰላም ግንባታ የምትሰጠው አስተዋጽኦ ቀርበው እንደተመለከቱ እና የሱዳን ቤተ ክርስትያን ወኪሎችዋን ወደ ተለያዩ አገሮች በመላክ ስለ ሱዳን እና ሊካሄድ ስለ ተወሰነው ሕዝበ ውሳኔ በተመለከተ የምትሰጠው መግለጫ የሁሉም አገሮች ብፁዓን ጳጳሳታ እና የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለሱዳን እንዲጸልዩ ማነቃቃቱ በማብራራት ያካሄዱት ጥረት በማድነቅ ቤተ ክርስትያን የፖለቲካ አካላት የሕዝብ ድምጽ በማዳመጥ እና ምላሽ መስጠት ተቀዳሚ አላማ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው በማሳወቅ፣ በጠቅላላ በሱዳን ያለችው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በአገሪቱ ሊካሄድ ተወስኖ ስላለው ሕዝበ ውሳኔ በእውነቱ ሕዝብ የራሱ ዕጣ ዕድል በገዛ ራሱ የመወሰን መብት እና ፍቃድ ተጠቃሚ ከመሆን የሚረጋገጥ እንጂ በወኪል የሚፈጸም መብት እና ፈቃድ አይደለም ካሉ በኋላ በዚሁ ረገድ በአገሪቱ ሊካሄድ ተውሰኖ ያለው የሕዝበ ውሳኔ የሕዝብ ፍላጎት ማረጋገጫ እንዲሆን በአፍሪቃ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና ምእመናን እንዲጸልዩ ያነቃቃ ስብሰባ ነው እንዳሉ ጉድ ኔውስ ረዲዮ ጣቢያ ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.